#6.
አደጋን የማያስከትሉ ሦስት አስፈላጊ አሰራሮች

የእራስዎ ስሜታዊ ደህንነት እንዴት የዚሁ አካል እንደሆነ ይረዱ

ለጭካኔ መጋለጥ በሚዲያ ባለሙያዎች ላይ ስሜታዊ ጫና ይፈጥራል። እራስዎን መንከባከብ ለራስዎ - እና ለምንጮችዎ ያለዎት ግዴታ ነው።

ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) መሸፈን ስሜትን የሚያደክም ስራ ነው፣ ይህም በአደገኛ እና ባልተረጋጉ አካባቢዎች ለሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች የግል አደጋዎችን ያስከትላል። የእራስዎን ጭንቀት ችላ ለማለት ሊያዳሉ ይችላሉ፣ ምክንያቱም ደግሞ መጠኑ ተጎጂዎችን እያጋጠሟቸው ካሉት ጋር ሲነጻጸር ትንሽ እንደሆነ ስለሚሰማዎ ነው። ቢሆንም፣ እነዚያ ትናንሽ ተጽእኖዎች ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊጨመሩ እና የበለጠ ችግር ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ይገነዘቡ፤ ይህም ከስራ ባልደረቦችዎ እና ከአደጋ ከተጎጂዎች በሚኖራቸው ግንኙነት ላይ ተጽዕኖ ሊያሳድሩ ይችላሉ።

ለአንድ ተጋላጭ ምንጭ ለወደፊት የማይጠበቁ ስሜታዊ ወይም የተግባር ድጋፍ እንዲሰጡ መገፋት፣ አንድ ጋዜጠኛ ወይም ፊልም ሰሪ መረጃው ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አንዱ ማሳያ ነው። ጉዳዮችን ከሌሎች ጋር ይነጋገሩ፤ የታሰበበት ራስን የመንከባከብ ስልት ይከተሉ እና ሌሎችን በመርዳት ረገድ ምን ማድረግ እንደሚችሉ እና እንደማይችሉ ግልጽ ይሁኑ።

ጥቁር አሜሪካዊው የዜጎች መብት ተሟጋች ኦድሬ ሎርድ በአንድ ወቅት እንዲህ ሲል ጽፏል፣

እራስን መንከባከብ ራስ መውደድ አይደለም። ራስን ማዳን ነው…

ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) መሸፈን ማለት የሰው ልጆች በሌሎች ላይ ሊያደርጓቸው የሚችሏቸውን አንዳንድ በጣም አስከፊ ነገሮችን መጋፈጥን ያካትታል። ጋዜጠኞች ራስን የመንከባከብ እና የስሜት-ቀውስ ግንዛቤን ለመወያየት ብዙ ጊዜ አያጠፉም፤ ምንም እንኳን ለህክምና ባለሙያዎች እና ሌሎች ከአደጋ ጋር ለሚሰሩ ሰዎች ቁልፍ አርእስት ቢሆንም።

መርሳት የሌለብዎት ነገር- እነዚህን ታሪኮች ለመዘገብ የሚፈልጉ ጋዜጠኞች እና የፊልም ባለሙያዎች ተነሳሽነት ያላቸው እና በጣም ጠንካራ ግለሰቦች መሆናቸውን ነው። ነገር ግን ይህ የሥራ መስክ ለድካምለድባቴ (ዲፕሬሽን)፣ አደንዛዥ እፆች አላግባብመጠቀም እና ከአሰቃቂ ሁኔታ በኋላ ለሚከሰት ጭንቀት ከፍ ያለ ስጋቶችን አሉት።[]ተጽኖዎቹ ብዙም ከባድ ባይሆኑም እንኳ፣ የሥራውን አሰቃቂ ይዘት በማወሃድ ላይ ያለው ችግር ቀድሞውኑ ተጋላጭ በሆኑ ምንጮች ላይ ተጽዕኖ ያሳድራል።

ርህራሄ እንደ ባለ ሁለት መንገድ ድልድይ

ከሌሎች ጋር በርህራሄ የመገናኘት ችሎታ እና ያሉበት የስሜታዊነት ደረጃ መለካት ውጤታማ ጠያቂ የመሆን አስፈላጊ ችሎታ ነው። ሰዎች ልምዳቸውን ለመካፈል በቂ ግንዛቤ እና ደህንነት የሚሰማባቸውን ሁኔታ የምንፈጥረው ርህራሄ በምናሳይበት ወቅት ነው። እንዲሁም በአንድ ታሪክ ውስጥ አስፈላጊ የሆነውን የምንረዳው እንዴት ነው – ነገሮችን በሌላ ሰው ጫማ [ሁኔታ] ውስጥ መቆም በመሞከር።

ርህራሄ በጠያቂውና ተጠያቂው መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ይከፍታል፤ ይህም ነገሮች ድልድዩን ተሻግረው ወደ ኋላ እና ወደ ፊት የሚሉበት መንገድ ይፈጥራል። ቃለ-መጠይቅ አድራጊ እንደመሆንዎ፣ እየሆነ ያለውን ነገር ሙሉ በሙሉ ሳያውቁ አንዳንድ ጊዜ ራስዎን የሌሎችን ስሜት ወስደው ሊያገኙት ይችላሉ። እንደ እፍረት፣ አቅመ ቢስነት እና ፍርሃት ያሉ ጠንካራ ስሜቶች ስውር እና ለመከታተል በሚከብዱ መንገዶች ተላላፊ ሊሆኑ ይችላሉ። ጋዜጠኞች ከአስጨናቂ ቃለ መጠይቅ በኋላ በራሳቸው ላይ በድንገት ማዘን ያልተለመደ ነገር አይደለም።

በተመሳሳይ፣ ሰዎች እንዴት እንደሚጠቁ ወይም እንደሚሰቃዩ ተደጋጋሚ ምስክርነቶችን በመስማት ወይም በማንበብ ያልተጠበቀ ጊዜ ውስጥ ጣልቃ የሚገቡ አስተሳሰቦች እና ምስሎች ወደ ጭንቅላት ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል። እነዚህ ተፅዕኖዎች አብዛኛውን ጊዜ ለአጭር ጊዜ እና በአንጻራዊነት ቀላል እና በተወሰነ ደረጃም ከስራው ጋር ተያይዞ የሚመጡ ናቸው – ነገር ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመሩ እና ሥር ከገቡ የአእምሮ ጤና መዘዝ ሊያስከትሉ ይችላሉ። ይህ ክስተት ‘ቪካሪዮስ (vicarious) ወይም ‘ሁለተኛ ስቃይ’ ተብሎ የሚጠራ ሆኖ ግጭትን በቀጥታ ከማየት ወይም ሰለባ ከመሆን ጋር ከሚመጡ ተጽእኖዎች ጎን ለጎን የሚከሰት ነው።

ወደ ሌሎች ሰዎች ጭንቀት መሳብ

ጋዜጠኞች በፍፁም ስሜታዊነት እንዲኖራቸው አይገባም የሚል ንድፈ ሃሳብ አለ። ይህ ቀልብ የሚስብ ሀሳብ ቢሆንም፣ ነገሮች ግን እንደዛ አይሠሩም። በተወሰነ ደረጃ ላይ ጠንካራ የመጨነቅ ስሜት እና የመርዳት ፍላጎት ሊሰማዎት ይችላል። ያ ከሆነ፣ እንደ ጋዜጠኛ ገደብዎ ማወቅና እና ድጋፍ ከማድረግ አንጻር ምን ማድረግ እንደሚችሉ እና እንደማይችሉ መወሰን በጣም አስፈላጊ ነው። ድንበሮች በሚጎዱ መንገዶች ሊደበዝዙ ይችላሉ፡-

  • ከሞያነት ይልቅ፣ የበለጠ ወዳጅነት ወዳለው አቅጣጫ መሳብ ሊሰማዎት ይችላል። የመርዳት ፍላጎት መኖር ችግር አይሆንም ነበር፤ ነገር ግን ሚናውን ለመወጣት የማይችሉ ከሆነ ከእውነታው የራቀ ነው። አደጋው፣ በማትወጣው እና የማያቋርጥ ስሜታዊ እና ቁሳዊ ድጋፍን ለማድረግ የውሸት ተስፋዎችን መገንባት ላይ ነው። ያስታውሱ፣ ባለማወቅ የሰዎችን ተስፋ መገንባት ቀላል ነው። የስሜት ቀውስ ባለበት ሁኔታ፣ እንደ መተሳሰር እና ክህደት ያሉ ጠንካራ ስሜቶች ሳይታዩ በውስጥ ነው የሚቆዩት። እንደ ጓደኛ ሳይሆኑ ሰብአዊነት ያለው ሰው መሆን እና በሥነ ምግባር መምራት ፍፁም ይቻላል።
  • የወሲብ ጥቃት በራስዎ ላይም የተፈጸመ ሊሆን ይችላል። ይህ ጠቃሚ ግንዛቤን ሊሰጥዎት ይችላል ነገር ግን የደረስዎት ጥቃት ምንጭዎ ከደረሳቸው ጋር የሚጣበቅበት ቦታ ላይ ሊጥልዎት ይችላል። ይህም ግን ሌላውን እንደ የተለየና ልዩ ሰው እንደሆነ የመረዳት ማስተዋልን እንዲያጡ ያደርጋቸዋል።
  • ቃለ መጠይቁ ለምንጭዎ በሆነ መንገድ የሚፈውስ (ቴራፒዩቲክ)፣ ስነልቦናዊ እርዳታ የሚሰጥ (ካታርቲክ)፣ ወይም ኃይልን የሚሰጥ ሂደት ሊሆን እንደሚችል ለማመን በመፈለግ ወጥመድ ውስጥ ሊወድቁ ይችላሉ። እውነት ነው ተጎጂዎች በመናገር መፅናናትን ያገኛሉ፣ ሰዎችን ግራ ከሚያጋባ እና የሚያሰቃይ አጋጣሚ የሚወጡበት አንዱ መንገድ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን እንደ ሚዲያ ባለሙያ ይህንን ሊያረጋግጡ የሚችሉበት ምንም መንገድ የለም። በእርዳታ ማህበረሰቡ ውስጥ፣ ይህ ‘የአዳኝ ውስብስብ’ ተብሎ ይጠራል፣ እና ከባድ ችግር ሊሆን የሚችል ነገር ነው።

የራስዎን ስሜት የመቆጣጠር ችግር ቃለ-መጠይቆችን ከሃዲዱ አስወጥቶ ወደ ሌላ አቅጣጫ ሊወስድ ይችላል። ለምሳሌ፣ ሰዎች እራሳቸውን ለመርዳት ብዙ ባለማድረጋቸው ልንበሳጭ እንችላለን፣ ወይም የሌሎችን ስቃይ ደረጃ መስጠት ልንጀምር እንችላለን፣ ይህ ደግሞ በጣም የከፋውን ብቻ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ሆኖ እንዲታይ የሚያደርግ ነው።

ለዚህ ሁሉ ምን ማድረግ ነው የሚሻለው?

መፍትሔው ርህራሄን ወይም ተልእኮውን መተው አይደለም። ሰው ሰራሽ በሆነ መንገድ የግል ስሜቶችን ማፈን አይጠቅምም። በተጨማሪ፣ ሁለቱም እራሳቸው የመቋቋም አቅም አካላት ናቸው። ይልቁንም ርህራሄን ከስልታዊ ዕረፍት የሚጠቀም ጡንቻ እንደሆነ አድርገው ያስቡ። ከስራው ገለል ብሎ መቆየት እይታን ያሰፋል፣ እንዲሁም ራስዎን ጉልበት እንዲያገኙና ከሚያሰቅቅ መረጃ ራቅ እንዲሉ የሚያስችል ዕድል ይሰጣል። ከአዎንታዊ የሕይወት ገጽታዎች ጋር እንደገና መገናኘት አስፈላጊ ነው። በዚህ ረገድ የሚከተሉት አንዳንድ ነገሮች ሊያግዙ ይችላሉ፡-

  • እራስዎን ከአስከፊ ነገሮች (እና በአጠቃላይ ስራን የሚያስታውስዎትን ማንኛውንም ነገር) እንዲያርቁ የሚያስችሉዎትን እንቅስቃሴዎችን በየቀኑ ይገንቡ። መሳጭ የትርፍ ጊዜ ማሳለፊያ፣ መጽሃፍ ማንበብ ወይም ጭንቅላትን ከርዕሱ የሚያወጣ ማንኛውም ነገር፣ ሁሉም ጥሩ ምርጫዎች ናቸው። ንቃተ-አእምሮ ለብዙዎች የሚሰራ ሌላው አማራጭ ነው።
  • መደበኛ እረፍቶችን እና የእረፍት ክፍለ-ጊዜዎችን ያቅዱ በማንደክምበት ጊዜ የሚያስጨንቁን ነገሮች በተሻለ መንገድ መቋቋም እንችላለን።
  • የሰውነትን ሚዛን ይጠብቁ። የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ዘርጋ ማለት፣ የአተነፋፈስ ልምምዶች፣ በቂ እንቅልፍ እና ተገቢ አመጋገብ ሁሉም እየተወጠረ እና እየጨመረ ያለዉ የጭንቀት መከማቸትን የማስወገድ ውጤታማ መንገዶች ናቸው።
  • ስለሚያስጨንቁ ጉዳዮች ከባልደረባ፣ አማካሪ ወይም ጓደኛ ጋር ይነጋገሩ። አንዳንድ ጊዜ ድምፅ የሚያጎላ ከሌለ ነገሮችን በግልፅ ማየት ከባድ ነው። ተመሳሳይ እርዳታ የሚፈልጉ ሌሎች ሰዎች ወደ እርስዎ የሚመጡ የሥራ ባልደረባ ከሆኑ፣ ችግሩን ለመመርመር ዕድል ከማግኘታቸው በፊት ችግራቸውን ለመፍታት ከመቸኮል ይልቅ ጥሩ አድማጭ ይሁኑ። ማስታወሻ እና ሌላ ግላዊ ጽሑፍ መጻፍም ሊረዱ ይችላሉ።
  • ከተፈጥሮ ጋር ግንኙነት ያድርጉ። በተለይ ይህ ብዙ ሰዎች ጠቃሚ ሆኖ አግኝተውታል።
  • ከስህተት-መማር የሚለውን አንታዊ አመለካከት ይከተሉ። ነገሮች ከተሳሳቱ፣ ከአደጋዎች እና ደካማ ውሳኔዎች ከመድገም ይልቅ ለመማር ይወስኑ።

ከላይ ከተዘረዘሩት ውስጥ አብዛኛው የመከላከያ ልማዶችን ስለመፍጠር እና ውጥረቶች በሚጨምሩበት ጊዜ እነሱን አለመተው ነው። በመስክ ላይ ሆነው እና መደበኛ ባልሆኑ ሰዓታት በሚሰሩበት ጊዜ እንኳን፣ በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎ ውስጥ አንዳንዶቹን መለማመድ ይችላሉ። ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ ማህበራዊ ድጋፍ ለመቋቋም ትልቁ አስተዋፅዖ ምክንያት ሊሆን ይችላል።[] ከመጠን በላይ ገለልተኛ ከመሆን እና ማንኛውም አይነት ከልክ ያለፈ ራስን የመፈወስ እርምጃዎች፣ በመድኃኒት ይሁን ወይም ከመጠን በላይ በመስራት ይጠንቀቁ። ሚዛን መጠበቅ ቁልፍ ነው።

ሽግግሮችን ማስተዳደር

የአገር ውስጥ ጋዜጠኛም ሆኑ ወይም ወደ አንድ አገር የሚገባ እና የሚወጣ የውጭ አገር ዜጋ፣ በሕይወትዎ ባለው አንጻራዊ የተሻለ መብትና እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ መካከል ያለው ልዩነት በተለይ ሽግግርን አስቸጋሪ እንደሚያደርግ ሊሰማዎት ይችላል።

በዚህ ርዕስ ላይ ከሚሰሩ የሚዲያ ባለሙያዎች መካከል የአቅም ማነስ (ስቃይ ለማስቆም የሆነ ነገር ማድረግ ባለመቻል) እና የጥፋተኝነት (ወደ ቤት መመለስ በመቻላቸው) ስሜት መኖር የተለመዱ ናቸው። ለእነዚህ አስቸጋሪ ሁኔታዎች ምንም ቀላል መልሶች የሉም፤ ነገር ግን እነሱን መጋፈጥ ተጠቃሚ መሆን ይችላል። ምናልባት እራስዎን እንዲህ ብለው ይጠይቁ፡- “ስለማልቆጣጠራቸው ነገሮች በራሴ ላይ ጫና መፍጠር ምንጮቼን መርዳት ወይም የበለጠ አስፈላጊነት ያለው ስራ መፍጠር ነውን?”

ለራስዎ ርህራሄ ሳይኖርዎት ለሌሎች ሩህሩህ መሆን ከባድ ነው። ርዕሱ በጨለመ ቁጥር፣ ወደ ኋላ መግፋት እና እርስዎን ብርታት የሚሰጡ ትናንሽ አወንታዊ ነገሮችን ለማግኘት መስራት የበለጠ አስፈላጊ ነው። እንደገናም፣ እነዚህን ጉዳዮች ከሚረዱ ሰዎች ጋር መነጋገር ሊረዳ ይችላል።

ተጨማሪ መረጃዎች: ራስን መንከባከብ

የዳርት ማእከል ከአሰቃቂ ምስሎች ያካተተ ስራ በሚመለከት ዝርዝር መመሪያ አለው። ጠለቅ ባሉ ምርመራዎች ወቅት አሰቃቂ ምስክርነቶችን ስለመቆጣጠር እና በህፃናት ወሲባዊ ጥቃት ታሪኮች ላይ በሰሩ ጋዜጠኞች እና የፊልም ሰሪዎች መካከል ስለራስ እንክብካቤ የተደረገ ውይይት ይህንን የታመቀ ጠቃሚ ምክር ይመልከቱ። በክፍል ቀ.1 እንደተጠቀሰው ሥራ አስኪያጆች ይህንን መመሪያ ሊመለከቱ ይችላሉ። ይህ የድረ-ገጹ ክፍል የአቻ ድጋፍን ሚና ጨምሮ ድርጅታዊ ጉዳዮችን በበለጠ ዝርዝር ይመለከታል።

እንነጋገር፡- የግል ድንበሮች፣ ደህንነት እና ሴቶች በጋዜጠኝነት (Personal Boundaries፣ Safety and Women in Journalism ) ለሴት ጋዜጠኞች ጾታዊ ትንኮሳን ስለመቆጣጠር ምክር ይሰጣሉ። ለድንበር-የለሽ ጋዜጠኞች (ሪፖርተርስ ሳንስ ፍሮንትይየርስ) ተብሎ በዳርት ሴንተር የተዘጋጀው ይህ ጠቃሚ ምክር በግጭት ቀጠና ውስጥ ለሚሰሩ ጋዜጠኞች የተለየ የራስ እንክብካቤ ምክር ይሰጣል። በመጨረሻም፣ የወሲባዊ ጥቃት ታሪኮች ብዙ ጊዜ በኢንተርነት መረብ ላይ ለሚገኙ በጥባጮች (ትሮልስ) እና ለሌሎች ክፉ ተዋናዮች የሚስብ ማግኔት በመሆናቸው፣ በዲጂታል ራስን-መከላከል ላይ አንዳንድ ሀሳቦች እዚህ አሉ።

]የግርጌ ማስታወሻዎች፡-