#7.
ዘገባውን ማቅረብ

ያስታውሱ፤ ጾታዊ ጥቃት መቼም ቢሆን የታሪኩ ብቸኛ ገጽታ አይደለም።

በክስተቶች ጭካኔ ላይ ብቻ ማተኮር ምንጮቹን እና ጋዜጠኘነትን ሊጎዳ ይችላል። ለክስተቱን ጠቅላላው ሁኔታ ትኩረት ይስጡ።

በጦርነት ውስጥ የጅምላ አስገድዶ መድፈር ወይም ጾታዊ ብዝበዛን የመሳሰሉ አስፈሪ ድርጊቶች ሲያጋጥም ትኩረቱን በጾታዊ ጥቃት እና በሚያስከትለው ጉዳት ላይ ማተኮር የማይቀር ሆኖ ሊታይ ይችላል። ነገር ግን የክስተቱ ሰፊነት ማምጣት አለመቻል ዘገባዎን የሚያሳንስ፣ ተመልካቾችን የሚያሳጣ እና የተረፉትን የሚያገል ነው። ታሪኩን በሚከተሉት መንገዶች ማስፋትዎን ያረጋግጡ፡-

  • የጉዳተኞችን ሕይወት በተመለከተ የተሟላ ዘገባ ይስጡ። መወደቅን ላለመተንበይ ወይም ሰዎችን ወደደረሰባቸው አስከፊ ነገሮች አሳንሰው እንዳያዩ ይጠንቀቁ። የማገገም ሂደታቸው ሊያወሳስበው ይችላል።
  • ከአስገድዶ መድፈር ያለፉ ሌሎች ወንጀሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ አስቡ። ጉዳተኞች የሚወዷቸው ሰዎች እና ቤታቸውን ሊያጡ እና በግዳጅ ሊፈናቀሉ ይችላሉ። እነዚህ ነገሮች ለሰዎችም አስፈላጊ ናቸው።
  • ለተጎጂዎች የሚሰጥ ህዝባዊ ርህራሄ ሊገድቡ ስለሚችሉ፣ ታሪኩን ወሲባዊ ስሜት ሊፈጥር ወይም ስሜት ቀስቃሽ እንዲሆን የሚያደርጉ ዝርዝሮች ላይ ከመጠን ያለፈ ትኩረትን ማድረግ ያስወግዱ።
  • ሙሉ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ሁኔታን በማቅረብ ተከታታዮችን የመፍትሄ አቅጣጫዎችን እንዲያዩ እርዷቸው።

ብዙ ጊዜ ምን ያህል ስራችን በጉዳተኞችን ህይወት ተመልሶ በሚድኑበት ሂደት ላይ ተጽእኖ እንደሚኖረው እንዘነጋለን።

ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ከከፍተኛ የስነ ልቦና እና የአካል ጉዳት ጋር የተያያዘ ነው። የጾታዊ ጉዳት መዘዝ ብዙውን ጊዜ ጠንካራ የመለያየት ስሜቶችን ያመጣል። ሰዎች ከራሳቸው እና ይህ ሁሉ ከመሆኑ በፊት ከነበሩት ሰው እንዲሁም ከሌሎች ጋር እንደተለያዩ ይሰማቸዋል። ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ከሰፊው ማህበረሰብ ጋር ያለውን ግንኙነት እንዲቋረጥ የማድረግ አቅም ስላለው፣ ጉዳተኞች እንዲገለሉ እና የድጋፍ እድሎችን እንዲቀንስ ሊያደርግ ይችላል።

በሌላ በኩል ማገገም የዚህን ተቃራኒ ይመስላል። ይህ መልሶ ግንኙነት በመፍጠር ሊሆን ይችላል- ሰዎች ሌሎች እነርሱን መንከባከብ እና በክብር መያዝ እንደሚችሉ ሲያምኑ።

እንደ ሚዲያ ሠራተኞች፣ ግለሰቦችን ማዳን የእኛ ድርሻ አይደለም። የእኛ ሥራ ጉዳተኞችን በግል መንገድ እንደሚያበረታታ መገመት ጥበብ የጎደለው እና እነሱን ዝቅ አድርጎ የሚያሳይ ነው- ይልቁንም ሳናስበው በእነዚያ የመለያየት ኃይሎች ላይ እንዳንጨምር መጠንቀቅ አለብን። በምስራቅ አፍሪካ የምትሰራ አሜሪካዊቷ ጋዜጠኛ ጂና ሙር እንዲህ ትላለች፡-

በምናወጣው ዘገባ ውስጥ – ከቀናት ፣ ወራት ፣ ዓመታት ብቅ ብሎ፣ እነሱን የሚያሸማቅቅ ወይም የሚያሰጋ ምንም ነገር እንደሌለ ማረጋገጥ አለብን. . .ዓለም ስለእነርሱ የሚያውቀውን እንዲገነዘቡ ለማድረግ የአሰቃቂዉን ታሪክ ዝርዝር ለተጎዱትን ደግመን እናብራራለን።[]

ለተመልካቾች የምንልካቸው መልዕክቶች እዚህ ወሳኝ ሚና ይጫወታሉ። በየቦታው ስለ ወሲባዊ ጉዳት ውይይቶች በአፈ ታሪኮች፣ መገለሎች እና የማይጠቅሙ አስተሳሰቦች የተሞላ ነው። እነዚህን ማጠናከር ሆነ ማጋለጥ እንችላለን – ጋዜጠኞች እና ፊልም ሰሪዎች በዚህ ጉዳይ ላይ ገለልተኛ ተመልካቾች አይደሉም። ለዚህም ነው የግጭቱ አጠቃላይ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ ገጽታዎች ላይ የተሟላ ዘገባ ማቅረብ አስፈላጊ የሆነው።

በአንድ የታሪኩ ጥግ ላይ የመጥፋት አደጋ

ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) በተለያየ መልኩ ይመጣል፣ ነገር ግን በጣም የሚስበው ባህሪው ብዙውን ጊዜ የጭካኔው ነው። በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ እንደ ፊልም ሰሪ ወይም ጋዜጠኛ፣ እርስዎ በሰሙት መጥፎ ነገር ተመልካቾችን ለማስደንገጥ፣ ይህ እንደሚያነቃቃቸው በማሰብ፣ ጠንካራ እና የማይገርም ፍላጎት ሊለማመዱ ይችላሉ።

ነገር ግን እዚህ ያለው አደጋ ይህ በተቃራኒውን ሊያሳካ ይችላል። በወሲባዊ ጥቃት አስፈሪነት እና ዝርዝር ላይ ብዙ ትኩረት መስጠት ተመልካቾችን ከግጭት ጋር በተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ለተጎዱ ሰዎች ያለውን ርህራሄ ሊቀንስ በሚችል መንገድ ከመከታተል ዘወር እንዲሉ ያስገድዳቸዋል። በቂ ተጨባጭ መረጃ ካላቀረቡ ተመልካቾች የእነዚህን ወንጀሎች ባህሪ እና የሚያስከትለው ነገር አይረዱም።

በግብፅ ውስጥ ጾታዊ ጥቃትን እና የመንግሥትን በፅናት ላይ ያለውን ሚና የሚዳስስ ለቫስ [መጽሔት] ፖድካስት መሰራች ስቴፋኒ ካሪዩኪ እነዚህ ውሳኔዎች ጥንቃቄ የተሞላበት ሚዛን ያስፈልጋቸዋል ይላል፡-

ምን ያህል ጠለቅ ብለን መግባት እንደምንፈልግ ለመወሰን ወዲህ እና ወዲያ ብለናል? ለምን ዝርዝሮችን እንሰጣለን፣ በእርግጥ አስፈላጊ ናቸው? በአንዲት ሴት ጉዳይ ላይ፣ የሕክምና መርማሪዎቹ በተለያዩ የመጀመሪያውን በደል በሚያንፀባርቁ  አኳኋን እንድትሆን በማድረግ እርቃኗን እያለች ብልቷን ደጋግሞ መረመሩ። የተጠቀምንበት የመጨረሻው ኦዲዮ ይህንን በግልጽ የሚሳይ ነው። ነገር ግን እኛ እንደዚህ ያህል በዝርዝር የገለፅንበት ምክንያት ይህ እሷ የምታደርገው ምርመራ እስከ አሁን ድረስ መንግሥት በሴቶች ላይ ለአሥርተ ዓመታት ሲያደርግ የነበረውን ሁኔታ የሚያሳይ ነው።[]

በእርግጥም፣ ስለአሰቃቂ ሁኔታ ውጤታማ ጽሁፍ ለማቅረብ እርስ በርስ የሚጋጩትን የተለያዩ ጉዳዮችን እንዴት ማመጣጠን እንደሚቻል ግምት ውስጥ ማስገባት ይጠይቃል። ለምሳሌ፡-

  • ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ምን ያህል በሰዎች ህይወት ላይ ጉዳት፣ አቅመ ቢስነት እና መቆጣጠር ማጣትን የሚያመጣው? ምን ያህል ስለ መቃወም እና ማገገም ነው- ለመትረፍ ምን ጠየቀ?

ምንም እንኳን ሁኔታው አስከፊ እና ተስፋ-ቢስ ቢመስልም፣ ጉዳተኞች በህይወታቸው ውስጥ አዎንታዊ ነገሮች አሏቸው። አስፈሪ እና ፍጹም አቅም ማጣት ብቻ በሰዎች ላይ ማንጸባረቅ ትክክልም ጠቃሚም አይደለም።

  • ምንያ ያህል ለአንድ ሰው ስለደረሰበት ግላዊ ክስተት ነው፣ ምንስ ያህል እና ስለ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታ፡ በተለይም ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ሁኔታዎች?

አጠቃላይ ሁኔታ ላይ በቂ ትኩረት ካልሰጡ፣ ታሪኩ ሰብአዊ ገጽታ ያለዉ አስገራሚ እና አስጨናቂ ሊሆን ይችላል – የትኛውም ትክክለኛ ዓላማ የሌለው እና ለተመልካቾች ምን እየተከሰተ እንዳለ ወይም መፍትሄዎች የት እንደሚገኙ ግንዛቤን የማይሰጥ ዓይነት። ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ምንም በሌለበት ውስጥ አይከሰትም – እንደ ርዕስ ‘በጦርነት ውስጥ መደፈር’ ግጭቱን የሚያንቀሳቅሱትን ኃይሎች ሳይጠቅስ ሊታወቅ አይችልም።

ነገር ግን ለግለሰቦች እና ለግል ሁኔታቸው በጣም ያነሰ ትኩረት መስጠት ክብር የጎደለው ሊሆን ይችላል፣ ምክንያቱም አንድ ሰው ለየት ያለ ቁጥር ለማሳየት ብቻ የተካተተ ነው የሚል ስሜት ሊፈጥር ይችላል።

ተቀናቃኝ ውጥረቶችን መደራደር

እያንዳንዱ ጉዳይ የተለያዩ ተከታታይ የማመጣጠን እርምጃዎችን ይፈልጋል። ይህንን መገንዘብ ብዙ ጊዜ የተወሳሰበ ነው ምክንያቱም ብጥብጥ መጥፎ ተጽዕኖ ሊያሳድር እና ቀሪው የማይጠቅም ወደሚመስለው አቅጣጫ ይጎትተናል። አስጊ እና አሰቃቂ ይዘት የሁለትዮሽ አስተሳሰብን ያስፋፋል፣ በዝርዝሮች ወይም በተገደቡ ማዕዘኖች ላይ መጣበቅ በጣም ቀላል ነው።

በሚጽፉበት ጊዜ ወይም በሚያድቱበት ጊዜ ግምት ውስጥ ማስገባት ያለብዎት አጭር የማረጋገጫ ዝርዝር እነሆ፡-

  • ይህ ከሚገባ በላይ ወደ አካላዊ ወይም ግላዊ (ወሲባዊ) ስዕላዊ መግለጫ የሄደ ነውን?
  • መግለጫውን ወሲባዊ የማድረግ አደጋ (እንዲያውም ባለማወቅ ለጥቃት መነሳሳትን ሰበብ) ሊሆኑ የሚያስችሉ የአንድን ሰው አካል፣ ገጽታ፣ ልብስ ወዘተ አሉ?
  • የእኔ ትረካ ወደፊት የአንድ ግለሰብ ወይም የማህበረሰብ ውድመት ይተነብያል? ምንም እንኳን ነገሮች ተስፋ-ቢስ ቢመስሉም፣ ማገገም የማይቻል መሆኑን መግለጽ ትክክል ያልሆነ እና አስቀድሞ መፍረድ ነው። (ከጨለማው ውጭ የሆነ ነገር ለማየት ከተቸገሩ እራስዎን ይህ ሰው ከደረሰበት ውጭ ማን እንደሆነ ይጠይቁ። ብርታት እና ድጋፍ ከየት ያገኛሉ?)
  • ወይም፣ በጣም ወደ ተቃራኒው አቅጣጫ እየዞርኩ ነው፣ እንዲሁም ተስፋ አስቆራጭ ሁኔታን በሰው ሰራሽ መንገድ ለማቃለል የውሸት ብሩህ ተስፋን እየሰጠሁ ነው? ከትክክለኛነቱ ውጭ፡ ብርታታትን የሚያጋንን ጋዜጠኝነት ሰዎች ያሉበትን የተገለጸውን ሁኔታ የማይገነዘቡትን ሰዎች ሊነጥል ይችላል።
  • የሰራሁት ዘገባ የሁለቱም የወንጀለኞች እና የተጎዱትን ድምጽ የሚያጠቃልል ከሆነ በእኔ ትረካ ውስጥ የወንጀለኞችን አመለካከት ማእከል የሚያደርግ ወይም ስልጣናቸውን የሚያሰፋ ነገር አለ? (ይህን በትክክል ማወቅ ውስብስብ ነው። እነዚህን ድምፆች ወደ ተለያዩ ዘገባዎች መለየት የበለጠ ቀላል ሊሆን ይችላል።)
  • የሰራሁት ዘገባ ሰዎች በግጭት ውስጥ የሚያጋጥሟቸውን ሌሎች አሰቃቂ ጉዳቶች በማግለል መደፈር ላይ ያተኩራል? ሰዎች ዘመዶቻቸው ሲገደሉ እና ቤታቸውንና መተዳደሪያቸውን ሲያጡ አይተው ይሆናል። አዲስ ሕይወት ለመገንባት የሚታገሉ ስደተኞች ሊሆኑ ይችላሉ። እነዚህ ሁሉ ነገሮች ለሰዎች አስፈላጊ ናቸው፣ ጋዜጠኞች የኪሳራዎቻቸውን አንድ ገጽታ ብቻ ማተኮራቸው ተጎጂዎች ላይረዱ ይችላሉ።

ታሪኩን ማቀናበር፡ ለአዘጋጆች የሚመለከቱ ማስታወሻዎች

አንድ ታሪክ የተቀነባበረበት መንገድ – ርዕሱ ፣ የፎቶ መግለጫዎች ፣ ፊልም ለማስተዋወቅ የሚያገለግሉ ምስሎች፣ ማጠቃለያ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ የቀረቡበት መንገድ – ታሪኩ እንዴት እንደሚታይ እና በእሱ ውስጥ በተካተቱት ሰዎች ውጤቱ ምን እንደሆነ ላይ ትልቅ ተፅእኖ ሊኖረው ይችላል።

አንድ ግልጽ አደጋ ታሪኩን ወሲባዊ ማድረግ ነው – እውነተኛውን አጠቃላይ ሁኔታን እውነተኛ እንዳልሆነ በሚመስል መልኩ ስሜት ቀስቃሽ ያደርገዋል። በወሲባዊ ጥቃት ውስጥ፣ ወሲብ ሊከሰት ይችላል – ነገር ግን እነዚህ ታሪኮች በምንም መልኩ ስለ መደበኛ ወሲባዊ እንቅስቃሴ አይደሉም።

እንደ ‘የወሲብ ባሮች’ ያሉ ቃላት ወሲብ ቀስቃሽ ስለሆኑ ጥቃትን ወደ መዝናኛነት የመቀየር አደጋ አላቸው። እንደ ‘የልጆች ሙሽሮች’ ያሉ አገላለጾች በተሻለ ሁኔታ እንደ ‘አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ጠለፋ እና ጾታዊ ጥቃት’፣ በሴተኛ አዳሪነት የተገደደች ሰው ‘የሴት ጓደኛ’ አይደለችም።

በላቲን አሜሪካ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) በሰፊው የፃፈችው ጂነት ቤዶያ፣ በነፍጠኞች የሚፈፀሙ የፆታዊ ጥቃት ዘዴዎች ተገቢ ካልሆነ እና ጊዜ ያለፈባቸው ቋንቋዎች እንዴት እንደሚሸፈኑ እዚህ ገልፃለች፡-

ጋዜጠኞች ስለ አስገድዶ መድፈርን ወይም ሴትን መግደልን ሲናገሩ ‘የስሜት ወንጀል’ ብለው ማውራትን ለማቆም በሚዲያ ዘንድ ብዙ ዘመቻ አድርገናል።

ህብረተሰቡ አሁንም አስገድዶ መድፈር አንዲት ሴት ሆን ብላ በአጥቂዋ ላይ ከምታነሳው የፆታ ቅስቀሳ ጋር የተያያዘ እንደሆነ አድርጎ ይቆጥራል። ስለዚህ ‘ስሜታዊ’ ተብሎ ይገለጻል። እንደ እውነቱ ከሆነ ግን እዚህ ያለው ቅስቀሳ፣ በዚህ ዓይነት ጋዜጠኝነት ውስጥ የተካተተው እንዲህ ዓይነት ወንጀሎች የሚፈጸሙት ‘በፍቅር’ ስም ነው የሚል ነው።

በብዙ የፍርድ ቤት ችሎቶች ውስጥ የሚደፍሩ ወንዶች በዚህ ክርክር እራሳቸውን ሲከላከሉ ሰምቻለሁ። ‘ስለወደዷቸው’ የፆታ ጥቃት እንደፈጸሙባቸው ወይም እንደገደሏቸው ይናገራሉ።

እንዲሁም አስገድዶ መድፈርን እንደ የማይቀር የጦርነት መዘዝ አድርጎ መቅረቡ ተረት መሆኑንም ልብ ይበሉ። የሚያስቀጣ የጦር ወንጀል ከመሆን በተጨማሪ፣ በሁሉም ግጭቶች፣ መደበኛ ያልሆኑ ተዋጊዎች በሚሳተፉበት ጊዜም እንኳ እንደማይስፋፋ ጥናቶች ያሳያሉ። []

እነዚህን ጉዳዮች ለማንፀባረቅ የእራስዎ የውስጥ ዘይቤ መመሪያ ማዘመን እንደሚያስፈልገው ያስቡበት። በቻሉ ጊዜ ሁሉ ለድጋፍ ድርጅቶች ግብዓቶችን እና ለማንኛውም የፆታዊ ጥቃት ሰለባ የሆነች ግለሰብ ጽሑፉን ለማንበብ ወይም ለማየት ጠቃሚ ሊሆን የሚችል መረጃን ያካትቱ።

ተጨማሪ መረጃዎች

በወሲባዊ ወጥመድ (In The Pornography Trap) በሚል ጽሑፏ ውስጥ ጂና ሙር ቋንቋውን ማስተካከል ስላጋጠሙት ተግዳሮቶች ተወያይታለች። ይህ ከቺካጎ ግብረ ኃይል በልጃገረዶች እና ወጣት ሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃትን (Chicago Taskforce on Violence Against Girls & Young Women) የመረጃ ስብስብ (Toolkit) በአጠቃላይ ስለ ጾታዊ ጥቃት ዘገባ ያብራራል እና የቋንቋ ምርጫዎችን የሚያንፀባርቅ ክፍል አለው።

ይህ ከብሔራዊ የፆታዊ ጥቃት መረጃ ማእከል (National Sexual Violence Resource Center) የወጣ የጥቆማ ወረቀት ሁሉንም አይነት ጾታዊ ጥቃቶችን የሚሸፍን ሆነ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ብቻ ያተኮረ አይደለም። ቢሆንም፣ ስታቲስቲካዊ አውድ-መር አካሄድን የመውሰድን ኃይል ያሳያል።

በዳርት ማእከል ድረ ገጽ ላይ ኒና በርማን አጠቃላይ ሁኔታን ግምት የማስገባት አስፈላጊነት እና ተገቢ የእይታ ምርጫዎችን በማድረግ ላይ ትዳስሳለች - ይህ ሁሉ በሚቀጥለው ክፍል በበለጠ ዝርዝር ተሸፍኗል።

]የግርጌ ማስታወሻዎች፡-

  • ሀ.

    በጂና ሙር ጽሑፍ፡ The Pornography Trap

  • ለ.

    ካሪዩኪ በዚህ ጥናት ተሳትፈዋል

  • ሐ.

    Carlo Koos (2017) Sexual violence in armed conflicts: research progress and remaining gaps፣ Third World Quarterly፣ available here.