በግጭት ወቅት ስለ ወሲባዊ ጥቃት መዘገብ
የተወሰኑ የጋዜጠኝነት ተግዳሮቶች በግጭት ወቅት የተከሰቱ ወሲባዊ ጥቃቶችን ከመዘገብ በላይ ኃላፊነትን ተሸክመዋል። በጦርነት ወወቅት አስገድዶ መድፈር ጥቅም ላይ ሲውል፣ በግለሰቦች እና በማህበረሰቦች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ አለው።
ኃላፊነት የሚሰማው ጋዜተኝነት ሰዎች ሊገልፁት በቂ ቃላት ላጡት እና ለተቸገሩበት ወንጀል ትኩረት እና አንጻር ያበጅለታል። ግድየለሽነት የተሞላበት ጋዜተኝነት በተቃራኒው፣ ተጎጂዎችን ለተጨማሪ አደጋ በማጋለጥ ጭንቀት እና ውጥረት ይጨምርባቸዋል። ይህ መመሪያ የተጻፈው በተደጋጋሚ በሲአርኤቪ ጋር ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ በሚሰሩ ጋዜጠኞች እና ፊልም ሰሪዎች ነው። መነሻውም እንደ ጋዜጠኝነት ተቋም ምርጥ ልምዶችን ለማጋራት እና የበለጠ ለመበየን በመፈለግ ነው። ግቡም የበለጠ ትክክለኛ እና የተሻለ ግንዛቤ የታከለበት ዘገባ ፣ ታሪካቸውን የሚናገሩ ግለሰቦች ከደረሰባቸው ጥቃት በላይ የሚደርስባቸውን ጉዳት በመቀነስ ማቅረብ እንዲቻል ለማድረግ ነው።
ከመጀመርዎ በፊት ራስዎን መጠየቅ ያለብዎት ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎች፤
አደጋን የማያስከትሉ ሦስት አስፈላጊ አሰራሮች፤
ዘገባው ማቅረብ፤