#1.
ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎች

ለዚህ በበቂ ሁኔታ ተዘጋጅቻለሁ?

በግጭት ቀጠና ውስጥ ስለ ወሲባዊ ጥቃት ከመገናኛ ብዙኃን ጋር መነጋገር ለማንኛውም የጥቃቱ ሰለባ የሆነች ሰው ከፍተኛ አደጋ አለው። እነዚህ መመሪያዎች አደጋው ምን እንደሆነ የተሻለ ግንዛቤ ይሰጡዎታል።

አንድ ጋዜጠኛ ከሚወስዳቸው በጣም ፈታኝ ሥራዎች ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) መዘገብ ቅድሚያ ይይዛል - ደግሞ በጥንቃቄ ማሰብን የሚጠይቅ ነው ። ሥራ ከመጀመርዎ በፊት የሚከተሉትን ገፅታዎች መመርመርዎን ያረጋግጡ።

 • ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ምን እንደሆነ እና አስገድዶ መድፈር እንዲሁም በሌላ መልክ የሚደርሱ ወሲባዊ ጥቃቶች በግለሰቦች እና በማህበረሰቦቻቸው የሚያሳድሩት ተጽዕኖ
 • አሰቃቂነቱ በሚያገናዝብ መልኩ እና ጥንቃቄ በተሞላበት መንገድ ተጎጂዎችን እንዴት ቃለ መጠይቅ ማድረግ እንደሚቻል
 • በአከባቢው ያለው ፖለቲካዊ ስልጣን እና አጠቃላይ የደህንነት ሥዕል፣ የሥርዓተ ፆታ ሁኔታዎች እና ስለ ፆታዊ ጥቃትን ያለ ባህላዊ አመለካከቶች
 • ሊያቀርቡት የሚፈልጓቸው ምስላዊ ምርጫዎች። የሰዎችን ፎቶግራፍ ያነሳሉ ወይም ቪድዮ ይቀርጻሉ? እንዴት እና የት ያደርጉታል? ስም-አልባ ይሆናሉ?
 • የራስዎ የስነ-ልቦና ዝግጁነት ደረጃ እና ለምን አስፈላጊ እንደሆነ

ይህንን መመሪያ የግጭት ግዜ ወሲባዊ ጥቃት ዘገባ ብለን ጠርተነዋል። ነገር ግን በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት የሚያመለክተውን መደበኛ የእንግሊዝኛ ምህፃረ ቃል CRSV እንጠቀማለን።

ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV)፣ ለምሳሌ፤ አስገድዶ መድፈር፣ አስገድዶ አዳሪነት፣ በአስገዳጅ ጋብቻ ውስጥ የሚደረግ ማምከን፣ እና ከግጭቶች ጋር ሊዛመዱ የሚችሉ ሌሎች ተመሳሳይ ወንጀሎች ያመለክታል። እነዚህ ወንጀሎች ብዙውን ጊዜ ወታደራዊ ወይም የፖለቲካ ግቦችን ለማሳካት ተብሎ ናቸው የሚፈጸሙት። ስለሆነም በሕጋዊ የዘር ማጥፋት እና የጦር ወንጀሎች ውስጥ ይካተታሉ። ነገር ግን አንዳንድ ግዜ፣ ድርጊቶቹ ዕድሉ በሚጠቀሙ ተራ ሰዎች ሊፈጸሙ ይችላሉ። ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV)፣ ‘በጦርነት ውስጥ የሚደረገው መድፈር’ ከሚለው ሐረግ በላይ በጣም የሰፋ ነው። ቃሉ፡ ታጣቂዎች፣ የጦር ኃይሎች ወይም የመንግስት ኃይሎች የአካባቢያቸውን ህዝብ ለመቆጣጠር እና ተዋጊዎችን ለማበረታታት ወሲባዊ ጥቃት የሚጠቀሙባቸው ሁኔታዎች ያጠቃልላል። በወንዶች እንዲሁም በሴቶች እና በልጆች ላይ ይፈጸማል።

እነዚህ ወንጀሎች ለተጎጂዎች እና ለማህበረሰቦቻቸው አስከፊ ውጤት አላቸው፣ ምክንያቱም CRSV ማህበራዊ ግንኙነቶችን በመበጠስ፣ ሰዎች ድጋፍን እና ድጋፍን ከሚሰጡ ከቤተሰብ፣ ከጓደኞች እና ከጎረቤቶች እንዲርቁ እና እንዲገለሉ ስለሚያደርግ ነው። በተጨማሪም ከመደፈር በኋላ ለሚወለዱት ልጆች ለትውልድ ሊዘልቅ የሚችል ጉዳት አለው። ወደ የማያቋርጥ መገለል እና ተጨማሪ ዓመፅ ሊያመራ ይችላል።

እንደ ጋዜጠኞች እና ፊልም ሰሪዎች ያለን ሚና

ብዙውን ጊዜ ተጎጂዎችን ለመጀመረያ ግዜ የሚያነጋግሩ የመገናኛ ብዙኃን አባላት ሲሆኑ፣ ይህን የሚያደርጉ ራሳቸው ለአደጋ በማጋለጥ ጭምር ነው፣ የህዝብና የመንግስት ግብረመልስ የሚጠይቁ ጉዳዮች ትኩረት እንዲያገኙ ማድረግ ስራቸው ስለሆነ። ይህንን ሥራ የሚሠራ ማንኛውም ጋዜጠኛ ምንጮቹ ላይ ጉዳት ማድረስ አይፈልግም፣ አደጋው እንዳለ ግን ግልጽ ነው። ምንም እንኳን ቀና ዓላማዎች ቢኖሩት፣ በቃለ መጠይቅ እና በዘገባው ላይ የሚደረጉ ስህተቶች ተጎጂዎችን ዋጋ እንደሌላቸው እና ብዝበዛ እንዲሰማቸው ማድረግ ይችላል። እንዲሁም ምንጮችን እና ቤተሰቦቻቸውን ለሀፍረት አልፎ ተርፎም በአንዳንድ ሁኔታዎች አካላዊ ጉዳያት ሊያጋልጡዋቸው ይችላሉ።

እ.ኤ.አ. በ 2018 አንድ ያልተለመደ ነገር ያከናወነ አንድ ዘገባ ታትሟል-በግጭት ዞን ውስጥ የ CRSV ሰለባ የሆኑትን ተጎጂዎች በመገናኛ ብዙሃን ቃለ መጠይቅ የማድረግ ልምዳቸው ምን እንደ ሆነ ጠየቀ። የተሰጡ መልሶች አሳሳቢ ነበሩ። ሰማንያ አምስት በመቶ የሚሆኑት፡ በዳርርት ማእከል የታተመ እና ተጎጂዎችን ለመጠበቅ በሚሠራ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ለጋዜጠኞች ተብለው የተዘጋጁት ሁለት ምርጥ የአሠራር መመሪያዎችን የሚቃረን አሰራሮች ያጋጠማቸው ነበሩ።[] በሪፖርቱ የተጠቀሱት ጉዳዮች የሚከተሉትን ያካትታሉ፤

የገንዘብ ወይም የእርዳታ ስጦታ በመጠቀም፣ ያለፈቃድ ማንነትን መግለፅ፣ ወይም የአስገድዶ መድፈር እና የወሲብ ጥቃትን ልምዶቻቸው ዝርዝር ለመግለጽ ግፊት ማድረግ… ስለ ጥቃቶቹ፣ በጣም ግላዊ እና ለሴቶች ተገቢ ያልሆኑ   ጥያቄዎችን በመጠየቅ ወይም ጋዜጠኞች የሴቶችን ታሪኮች በማተም የያዚዲ ማህበረሰብን ለመርዳት በሚስችላቸው ሁኔታ ላይ መሆናቸውን መጠቆም።[]

የአደገኛ አካባቢ ሥልጠና- በከፍተኛ የአደጋ ሁኔታዎች ጋዜጠኞች የራሳቸው ደህንነት እንዲጠብቁ ማዘጋጀት- አሁን የተለመደ ነው፣ ነገር ግን አብዛኛዎቹ ሪፖርተሮች አሁንም ከአሰቃቂ ሁኔታ ተጎጂዎች ጋር ለመስራት ተገቢ ሥልጠና አያገኙም፣ ሊጠቀሙበት የሚችሉ መመሪያም ብዙ የለም።

ለመሆኑ ጥሩ ዝግጅት ምን ይመስላል?

በማንኛውም የመዘገብ ጉዞ ላይ፣ በተለይም ወደ ከፍተኛ አደጋ ያለበት አካባቢ የሚደረግ፣ ጊዜ በጣም ወሳኝ ነው ፣ ስለዚህ ይህን ለማድረግ በሚቻልበት ወቅት ስለእነዚህ ነገሮች አስቀድመው ማሰብ ተገቢ ነው። ዝግጅት በሁለት ዋና ዋና መልክ ይካሄዳል፣ ሁለቱም ደግሞ ወሳኝ ናቸው፤

 1. ለተለየ ተልእኮ በሚመደቡበት ወቅት ከበሩ ከመውጣትዎ በፊት ማድረግ ያለብዎት ዓይነት። ይህ አካባቢያውን ማጤን፣ የአደጋ ግምገማዎችን እና የመሳሰሉትን ያጠቃልላል።
 2. ክህሎቶችን ለማዳበር የረዥም ጊዜ ቁርጠኝነት መኖር። ይህ ከስልጠና፣ ጉዳዮቹን ለመረዳት ቁርጠኝነት እና ከሌሎች የሥራ ባልደረቦች ጋር ግንዛቤዎችን ለማካፈል የመስጠት እና የመውሰድ የተከፈተ ዓዕምሮ መኖር የሚመጣ ነዉ።

ለተመደቡለት ልዩ ስራ የሚመለከት ዝግጅት

ለራስህ እና ለቡድንህ ደህንነት የአደጋ ምዘናዎችን የማካሄድ ልምድ ሊኖርህ ይችላል። (ከታች ያለውን የመረጃ ሳጥን ይመልከቱ።) በተመሳሳይ ጊዜ፣ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃትን (CRSV) በሚሸፍኑበት ጊዜ፣ ዘገባዎ ከእርስዎ ጋር የሚሰሩትን የማንኛውም ምንጮች አካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ደህንነትን እንዴት ሊጎዳ እንደሚችል ማሰብ አለብዎት።

መጠየቅ ያለብዎት ጥያቄዎች፡

 • ስለራስዎ ደህንነት ብቻ ሳይሆን ቃለ ምልልስ ስለምታደርጉት ሰዎች ደህንነትም ጥሩ ውሳኔዎችን ማድረግ በሚያስችል ደረጃ የአካባቢ የስልጣን ዳይናሚክስ እና በመሬት ላይ ያለውን የደህንነት ሁኔታ አጥንተውታል? [ቁ.2 ይመልከቱ]።
 • ከተጎጂዎች ጋር የሚያደርጉትን ቃለ መጠይቅ ማን ያመቻችልዎታል? አገናኝ፣ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይስ በአከባቢው የስልጣን ተጽዕኖ ያላቸው ወገኖች? መስማማታቸው በፈቃደኝነት ላይሆን የሚችልበት አደጋ አለ? [ቁ.2 እና ቁ.3 ይመልከቱ]።
 • ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ማዕቀፉን ተረድተዋል – ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት አካባቢያዊ አመለካከቶች፣ በጾታ ላይ የተመሰረተ መድልዎ እና በቤተሰብ ውስጥ ያለውን የስልጣን አለመመጣጠን ጭምር? ለተሳታፊዎቹ ሊያስከትለው የሚችል አደጋ በሚገባ ተረድተዋል? [ቁ.2 ይመልከቱ።]
 • በአካባቢው ስላሉ የአካባቢ ህጎች፡ ይፋ ማድረጉ ከምንጮች ደኅንነት እና ተጨማሪ የፍትህ ዕርምጃ ለመፈለግ ባላቸው ችሎታ ላይ ሊያመጣ የሚችለውን አንድምታ ተገንዝቦውታል? (በአንዳንድ ክልሎች የአስገድዶ መድፈር ሰለባ መሆን ብቻ የዝሙት ክስ ሊቀርብ ይችላል።)
 • ስለራስዎ የስነ-ልቦና ዝግጁነትስ? አሁን ይህንን ስራ ለመስራት በግልዎ ጥሩ ሁኔታ ላይ ነዎት? [ቁ.6 ይመልከቱ]።

መደበኛ ዝግጁነት

አንዳንድ ሌሎች የዝግጅት ዓይነቶች ረዘም ያለ ግዜ ስለሚያስፈልጋቸው፣ ወደ ስራ ከመሰመራቱ በፊት በደንብ ታቅደው ቢቆዩ ይሻላል። እንዲሁ፣ በተዛማጅ ሥልጠና ላይ መሳተፍ ግድ ይላል፣ ካልሆነ ግን፣ እንደ ራስዎ-ማስተማር ወይም ከዕውቀት ካላቸው ባልደረቦች ውጤታማ ምክር ያሉ ሌሎች መንገዶች ሁሉንም ሊያግዙ ይችላሉ።

ራስዎን ይህንን ይጠይቁ፤

 • የምንጮችን ስም-አልባነት ለመጠበቅ እና ጥድፊያዎችን ለመጠበቅ ብቁ የዲጂታል ደህንነት እቅድ አልዎት? [የመርጃ ሣጥን ቁ.2ን ይመልከቱ]።
 • የጾታዊ ጥቃት ሰለባ ለሆኑ ጉዳተኞች ቃለ መጠይቅ ለማድረግ የሚረዱ ስልቶችን ለማግኘት ጥናት አድርገዋል? እዚህ ማወቅ ያለብዎት ልዩ ጉዳዮች አሉ። [ቁ.4 እና ቁ.5 ይመልከቱ]።
 • ትርጉም ያለው ስምምነት የሚለውን ሃሳብ ተረድተውታል፣ እንዴት ማቅረብ እንዳለቦትስ አስበውበታል? [ቁ.3 ይመልከቱ]።
 • ቪድዮ ወይም ፎቶግራፍ የሚያነሱ ከሆነ፣ ስም-አልባነቱ እንዴት እንደሚይዙት እና ተጎጂዎችን ብጥሩ ሁኔታ እንዴት ማስተናገድ እንደሚችሉ አስበውበታል? [ቁ.8 ተመልከት]።

አዘጋጆች ሊያስቡበት ያላቸው ነገሮች

እነዚህ መመሪያዎች ለማዘጋጀት ባካሄድናቸው የምክክር ሂደት ወቅት ያነጋገርናቸው ሁሉም – አዘጋጆችም ሆኑ ሪፖርተሮች፣ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃትን (CRSV) የታዩባቸው እና ከነሱ ውጭ በሆኑ አገሮች – አዘጋጆች እና የፊልም ተልእኮ የሚሰጡ ሃላፊዎች ምንጮችን በመጠበቅ ረገድ ያላቸውን ሚና አጉልተዋል። በመሬት ላይ ያሉ ጋዜጠኞች በዘፍቃድ አይሰሩም: ተጠሪነታቸው ለህትመቶች ወይም ለብሮድካስተሮች ናቸው።

በጠረጴዛው እና በመስክ መካከል ያለው ግንኙነት ግን ትልቅ ችግር ሊሆን ይችላል። በጣም ጥሩ በሆነው ሁኔታ፣ የዜና ክፍሉ ከክስተቶች ያለው ርቀት ዜናውን ከስሜት በራቀ እንዲገመግም ያደርገዋል። ነገር ግን በነባራዊ ሁኔታን እና  በተጎጂዎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ያለው ግንዛቤ አናሳ እንዲሆን ሊደርግም ይችላል። አንዳንድ ጊዜ በመስኩ  ውስጥ ያሉ ጋዜጠኞች የተከፈለ ተከፍሎ ዜናውን እንዲያገኙ ጫና አለባቸው።.

በተመሳሳይ መልኩ፣ አዘጋጆቹ በመሬት ላይ ስለሚሆነው ነገር ሙሉ ቁጥጥር የላቸውም። ጋዜጠኞች እና ፊልም ሰሪዎች ብዙውን ጊዜ በከፍተኛ ጫና ውስጥ እየሰሩ ናቸው እናም ብዙ ርቀት ተጉዘው በከፍተኛ የግል ስጋት ውስጥ ሊሆኑ ይችላሉ; ፍሪላንስ ጋዜጠኞች ወደ ግጭት ቀጠና ለመድረስ የራሳቸው ገንዘብ አውጥተው ሊሆን ይችላል። በነዚህ ሁኔታዎች ማዕዘኖች ሊቆረጡ ይችላሉ፡ ቃለመጠይቆች ከሚገባቸው በላይ ሊመዘመዙ ይችላሉ፣ በትክክል በመረጃ ላይ የተመሰረተ ስምምነት ላይገኝ ይችላል፣ ወይም የተጎጂዎችን ስም-አልባነት እንዳይጋለጥ ለመከላከል በቂ እርምጃ ላይወሰድ ይችላል።

የተሻለ ግንኙነት መፍጠር ከእነዚህ ብዙ አደጋዎችን ለማስወገድ ይረዳል። ጋዜጠኞች የሚገጥምዋቸው የስነምግባር ጉዳዮችን ከአዘጋጆች ጋር ማካፈል እንደሚችሉ ነጻነት ሊሰማቸው ይገባል። በተጨማሪ ዜናውን ለማግኘት ከህትመቱ አላማ በፊት የተጎጂዎችን አካላዊ እና ስሜታዊ ደህንነት በማስቀደማቸው ቅጣት እንደማይደርስባቸው ሊሰማቸው ይገባል።

በመመሪያው ውስጥ እነዚህን ጉዳዮች በጥልቀት እንመረምራለን። ከዛ በፊት ግን፡ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃትን (CRSV) ለመዘገብ ጋዜጠኞችን ለየሚያሰማሩ አዘጋጆች አጭር ማረጋገጫ ዝርዝር እንሆ፡

 • ጋዜጠኞች፣ ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑ ሰዎች ጋር በሚሰሩበት ግዜ ሊከተሏቸው የሚገቡትን ·àò·à†·à®·â≥ãä
 • ህጎች ተወያይተዋል?
 • የምንጮችን ማንነት እና ክብር ለመጠበቅ አስፈላጊ ለሆኑ የእይታ ምርጫዎች በሚመለከት ተገቢ እቅድ አውጥተዋል? በዛን ጊዜ ለመወሰን ቀላል አይደለም።
 • ይህንን ጋዜጠኛ ለዚህ ስራ መመደብ አሁን ትክክል ነው? በተከታታይ ብዙ አሰቃቂ ስራዎችን በመሸፈን ከመጠን በላይ የመጫን አደጋ አለው ወይ?
 • ጋዜጠኛው ከእርስዎ ጋር ማንኛውንም የስነምግባር ጉዳዮች መወያየት እንደሚችሉ ያውቃሉ?
 • ጋዜጠኛው ይህን የመሰለ መረጃ አግኝተዋል?
 • እና በመጨረሻም፣ ተጎጂዎችን እንዴት ቃለ መጠይቅ ማድረግ እንደሚቻል የሚመለከት ተገቢውን ስልጠና ለመስጠት አስበሃል? መጥፎ አጋጣሚ ሆኖ፣ ይህ በአብዛኛው የአደገኛ አካባቢ ስልጠና ውስጥ የሚካተት ነገር አይደለም። ከአሰቃቂ ክስተቶች ጋር በተያያዙ ስራዎች ላይ የሚሰማሩ ጋዜጠኞችን ለመደገፍ እና ለመጠበቅ ድርጅትዎ ምን ማድረግ እንደሚችል በዚህ በዳርት ሴንተር ኤዥያ ፓሲፊክ የተዘጋጀ መመሪያ ውስጥ ተጨማሪ ማግኘት ይችላሉ።

ክፍል ቀ.7 እና ቁ.8 ስለ ሕትመት እና ስርጭት ጉዳዮችን በበለጠ ዝርዝር ያብራራሉ።

ተጨማሪ መረጃዎች፤ አጠቃላይ እይታ

በመጀመሪያ፣ ሁሉም ሰው የሙራድ ኮድን ረቂቅ እንዲያነብ እናበረታታለን። ይህ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃትን (CRSV) ተጎጂዎች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ላለው ማንኛውም ሰው የምርጥ አሰራር መርሆዎችን አጥርቶ የሚያሳይ ተነሳሽነት ነው - ጋዜጠኛ፣ ጠበቃ፣ የወንጀል መርማሪ፣ ፖሊሲ አውጪ ይሁኑ ወይም መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ጠበቃ። ከተጎጂዎች እንዲሁም ከባለሙያ አካላት ጋር በጥልቀት የተደረገ የመመካከር ውጤት ነው።

የዳርት ሴንተር የወሲብ ጥቃትን ለመሸፈን ብቻ የሚያተኩር ክፍል በድረ-ገጹ አለው። እዚያ፣ አጠቃላይ እይታን የሚያቀርብ ይህን የዳርት ሴንተር አውሮፓ የምክር ገጾች ማግኘት ይችላሉ።

የአደጋ ግምገማ እና እቅድ መረጃዎች በክፍል ቁ.2 ውስጥ ተካትተዋል።

የግርጌ ማስታወሻዎች፡-