#2.
ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎች

ይህንን ሰው በዚህ ጊዜ እና በዚህ ቦታ ቃለ መጠይቅ ማድረግ አለብን?

የምንጮች ደህንነት መገምገም በሁሉም ደረጃ ያሉ ጋዜጠኞች ኃላፊነት ነው - በመሬት ላይ ያለው ዘጋቢ ይሁን፣ በዜና ክፍል ውስጥ ያለው አዘጋጅ እና ተመሳሳይ ዘገባ ለመስራት የሚፈልጉ ባልደረቦች።

ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV)ን በሚዘግቡበት ጊዜ ጋዜጠኞች ለራሳቸው እንደሚያደርጉት በምንጮቻቸው ደህንነት ላይ የአደጋ ግምገማ ማድረግ አለባቸው። ስለ ተገቢ ጥንቃቄ ያሉ ዋና ጥያቄዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፤

 • ይህንን ቃለ መጠይቅ ተገቢ ብሆነ መንገድ ለመምራት በቂ ጊዜ አለኝ? እነዚህ ንግግሮች በችኮላ መደረግ የለባቸውም። ካልሆነ፣ ምንም አይነት ጉዳት ላለማድረግ ነገሮችን በተለየ መንገድ እንዴት ማድረግ እችላለሁ?
 • ይህ አካባቢ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው? በክፍሉ ውስጥ ያለው ማን ነው እና ማንስ ውስጥ መሆን የለበትም? በእኔ ምንጭ ላይ ሊያስከትል የሚችለውን መዘዝ ለመገምገም የኃይሉን ተለዋዋጭነት በበቂ ሁኔታ ተረድቻለሁ? የማስገደድ ስሜት አለ?
 • ይህ ሰው ለማነጋገር ትክክለኛው ሰው ነው? እሷ፣ እሱ ወይም እነሱ በስሜታዊነት በዚህ ጊዜ ለዚህ ውይይት በቂ የተረጋጋ ነው? ካልሆነስ ማን ሊሆን ይችላል?

ከፍተኛ የግል ስጋት በተመለከተ ረጅም ልምድ ሊኖርብዎት ይችላል፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ የሁኔታው ስነምግባር አዲስ እቅድ ሊያስፈልግ ይችላል። አዘጋጆች ሆኑ በመስክ ላይ ያሉ ሰዎች ለዚህ ሃላፊነት መውሰድ አለባቸው - መነጋገር ጠቃሚ ይሆናል?

ይህን ለማድረግ በቂ ጊዜ አለኝ?

ጋዜጠኞች በስራቸው ከፍተኛ የጊዜ ግፊት አለባቸው። ነገር ግን የከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ተጎጂዎችን አሰቃቂነት ግምት ውስጥ ባስገባ ሁኔታ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ በቂ ጊዜ መስጠት አለቦት።

 • ከተጎጂዎች ጋር ተገቢ በሆነ መልኩ ቁጭ ብለው ለመነጋገር ጊዜ ሊኖርዎት ይገባል.
 • በቂ ጊዜ ከሌለዎት ቀንዎን እንደገና ማቀድ ይችላሉ?
 • ቃለ-መጠይቁን በተለየ መንገድ ማድረግ ይችላሉ – ለምሳሌ፣ ስለያጋጠማቸው አሰቃቂ ዝርዝሮችን እንዲናገሩ ከመቸኮል ይልቅ በማስረጃ የተደገፉ ጥያቄዎችን በመጠየቅ?
 • በቀጥታ ካልተጠቃ ታማኝ ምንጭ ጋር መነጋገር ይችላሉ?

የዚህ ዓይነቱ እቅድ ከእርስዎ እና ከተጎጂዎች ውጭ ያሉ ሌሎች ሰዎችን ሊያካትት ይችላል። ቃለ መጠይቁ እንደ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም የአገር ሽማግሌዎች ቡድን በመሰለ አማላጅ በኩል እየተዘጋጀ ከሆነ፣ አቀራረባችሁን በዚሁ መሠረት ማቀድ እንዲችሉ ምን ያህል ጊዜ እንደሚኖሮት ከአዘጋጁ ጋር ይነጋገሩ።

በተቻለ መጠን በዚህ እቅድ የማውጣት ሂደት ተጎጂዎችን ማካተት አለቦት። የእራስዎ የጊዜ ሰሌዳ ተለዋዋጭ ከሆነ፣ በተለይ ስለሚያሰለች ጉዳይ ለማውራት ብዙ ጉልበት ሊኖራቸው የሚችልበት ጊዜ ካለ አስቀድመው ጠይቋቸው። ተለዋዋጭነትን ወደ ምንጩ መመለስ ታሪካቸውን ለማካፈል የተወሰነ ቁጥጥር እንዳላቸው እንዲሰማቸው በማድረግ ረገድ ቀላል ግን ኃይለኛ መንገድ ነው።

ይህ ቦታ ለቃለ መጠይቅ አስተማማኝ ነው?

በምትሠሩባቸው አካባቢዎች ስለሚኖር አካላዊ ደህንነት ለማሰብ ተለማምደው ይሆናል። ነገር ግን ተጎጂዎችን ቃለ መጠይቅ ለማድረግ እቅድ ካልዎት፣ ይህን ሃሳብዎ ወደ ላቀ ደረጃ መውሰድ አለብዎት። በክፍሉ ውስጥ ያለው ማን ነው እና ለምንን የሚሉ አንዳንድ ቀላል ጥያቄዎችን እራስዎን በመጠየቅ ይጀምሩ፡

 • የማህበረሰብ ሽማግሌዎች፣ ባለስልጣኖች ወይም ጠመንጃ ያላቸው ሰዎች አሉ?
 • ከወንጀለኞች ጋር በሚገናኝ መረብ አካል የሆኑ ሰዎች አሉ?
 • እዚያ መገኘት የማያስፈልግ ሰው አለ?

የጥቃት ፈጻሚዎች በክፍሉ ውስጥ ባይኖሩም በህብረተሰቡ ውስጥ እየኖሩ ነው? ስለ ቃለ መጠይቁ ሊሰሙ ይችላሉ? ቦታው ምን ያህል ገለል ያለ ነው? ጉዳተኞች ከማህበረሰቡ፣ ከቤተሰብ አባላት እና ከመሳሰሉት ወገኖች ሊገጥማቸው የሚችለው ተጨማሪ መገለሎችን ለማስወገድ ምን ማድረግ ይችላሉ?

ምን እየሰሩ እንደሆነ በትክክል ካላወቁ በስተቀር ሰዎችን ዓመጹ ወደ የተፈጸመበት ቦታ አይውሰዱ። የቦታ እና የእይታ ትውስታዎች ከፍተኛ የስሜት ቀውስ ሊያስከትሉ ይችላሉ።

ምንም እንኳን እንደዚህ አይነት ሁኔታን ለማስታረቅ አስቸጋሪ ሊሆን ቢችልም, ቃለ-መጠይቁን እርስዎ የሚቆጣጠሩት እንደሆኑ ያስታውሱ። ስለዚህ የተገደዱ መስለዉ ከታዩ, ወይም ተጎጂዎችን አደጋ የሚያስከትል ከሆን ወደ። መቀጠል የለብዎትም። አዘጋጆችም እዚህ ላይ ሚና አላቸው፣ ምክንያቱም ጋዜጠኛው የስነምግባር ፈተና በሚገጥመው ግዜ ከዜና ክፍል የሚመጣ ግፊት አእምሮው ላይ ስለሚመዝን።

ከእርስዎ ጋር የመጡ ሰዎችም ሊኖሩ ይችላሉ፡-

 • አሰራጭ ከሆኑ የረዳተችዎን ቁጥር አነስተኛ ማድረግ ይችላሉ?
 • ከፎቶግራፍ አንሺ ጋር እየሰሩ ከሆነ, ተጎጂውን ስለ አሰቃቂ ክስተቶች ሲናገር በተመሳሳይ ጊዜ ፎቶግራፍ እንዳይነሳ ለማድረግ፡ ፎቶግራፎቹን በተለየ ግዜ ወይም ከቃለ መጠይቁ በኋላ ማንሳት ይችላል?
 • ከአስተርጓሚ ጋር እየሰሩ ከሆነ, ለሥራው ትክክለኛ ሰው ናቸው? ጉዳዮቹን ተረድተዋል? ስለ አሰቃቂ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ ቃለ መጠይቅ ገለጻ ተሰጥቷቸዋል?
 • ተጎጂው በክፍሉ ውስጥ ከተቃራኒ ጾታ ካላቸው ሰዎች ጋር መነጋገር ምቾት ይሰማዋል? ሴቶች ሴቶችን ቃለ መጠይቅ ማድረግ፣ ወይም ወንዶች ለወንዶች ቃለ መጠይቅ ማድረግ የግድ አስፈላጊ አይደለም፣ ነገር ግን ይህ ግምት ውስጥ የሚገባ ነው።
 • ከተቻለ ተጎጂዎችን ምን እንደሚያመቻቸው ይጠይቁ። ከሳቸው ጋር እንዲሆን የሚፈልጉት እንደ ዘመድ ወይም ታማኝ ወዳጃቸው ሰው አለ? ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን ቃለ መጠይቅ እያደረጉ ከሆነ፣ ሞግዚታቸው ሁል ጊዜ መገኘት አለበት። (ስለ ወሲባዊ ጥቃት ልጆችን እና ወጣቶችን ቃለ መጠይቅ ማድረግ የተወሰኑ ክህሎቶችን እና ተጨማሪ ትጋትን ይጠይቃል። ይህ በእርግጥ ማድረግ ያለብዎት ነገር እንደሆነ እራስዎን ይጠይቁ።)

ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ትክክለኛው ሰው ይህ ነው?

እነዚህን ቀላል ጥያቄዎች ይጠይቁ፡-

 • ይህን ቃለ መጠይቅ ማድረግ ያስፈልጎታል? የሚጨምረው ነገር አለ ወይም አስቀድሞ ያገኙት በቂ መረጃ አለ?
 • ተጠያቂዎች ምን እንደሚጠበቅባቸው በሚረዱበት ሁኔታ ናቸው ያሉት?
 • የተደበቁ ተስፋዎች አሉ? ከእውነታው የራቁ ያልሆኑ ከእርስዎ ጋር በመገናኘት ውጤቱን እየጠበቁ ነው?
 • የሆኑ የተደበቁ ተስፋዎች አሉ? ከእርስዎ ጋር በመገናኘታቸው ከእውነታው የራቁ ውጤቶች እየጠበቁ ነውን?

ብዙ ጊዜ በግጭት ወይም ከግጭት በኋላ ባሉ ሁኔታዎች፣ በመሬት ላይ የሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የጋዜጠኞች መዳረሻ ናቸው፣ እና እርስዎ ከፆታዊ ጥቃት የተረፉ ሰዎችን እንዲያነጋግሩ የሚያዘጋጁት እነሱ ሊሆኑ ይችላሉ። መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አንድ ሰው ወይም ትንሽ ቡድን ከጋዜጠኞች ጋር በሚያጨናንቅ ቃለ ምልልስ እንዲሳተፉ በማድረግ የሚያዘጋጁበት ሁኔታ ሊገጥሞት ይችላሉ። በአጭር ጊዜ ውስጥ ታሪኩን ደጋግሞ መናገር አሰቃቂ ጉዳት ለደረሰበት ሰው በጣም የሚያስጨንቅ ሊሆን ይችላል። እንዲሁም በተረፈው ላይ ህጋዊ መዘዝ ሊኖረው ይችላል። የሰጡት የተለያዩ ቃለ መጠይቆች በጥቂቱ የሚቃረኑ ከሆነ፣ በኋላ ላይ የሕግ ዕርምጃ የመፈለግ እድላቸውን ሊያሳጣው ይችላል [ሳጹን ቁ.3 ይመልከቱ]።

ጋዜጠኞች ካላቸው ጫና አንፃር፣ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከሚሰጡት ምክር ጋር አብሮ መሄድ ቀላል ነው። ነገር ግን ቃለ መጠይቅ በሚያደርጉት ማንኛውም ተጎጂ ላይ ስለሚኖሩ ጫናዎች ውይይት ማድረግ ጠቃሚ ነው። ምን ያህል ጊዜ ቃለ መጠይቅ እንደተደረገላቸው መጠየቅ ሊሆን ይችላል። እና በፈጠራ አስቡ – በጋዜጠኞች ቡድን ውስጥ እየተጓዙ ከሆነ፣ ተጎጂዎችን ታሪካቸውን አንድ ጊዜ ብቻ እንዲያካፍሉ ጥናቶቻቹህ በአንድ ማሰባሰብ ይቻላል?

እ.ኤ.አ. በ2019፣ የሂዩማን ራይትስ ዎች ሰራተኛ የሆነች ስካይ ዊለር በ’ኮሎምቢያ ጆርናሊዝም ሪቪው’ የተባለ መጽሔት እንደጻፈችው በባንግላዲሽ በሚገኙ የሮሂንጊያ የስደተኞች መጠለያ ካምፖች ከሚገኙ የፆታዊ ጥቃት ሰለባ የሆኑ ሰዎች የተደረገ ስነ-ምግባር የጎደለው ጋዜጠኝነትና እና የምርምር አሰራሮች ላይ አንፀባርቃለች፡-

“ያለ ጥርጥር፣ ወደ ኋላ መለስ ብለን ስናስብ ነገሮች ጥሩ አልነበሩም ማለት እንችላለን። ሰዎች በጣም ብዙ ጊዜ በድጋሚ ቃለ መጠይቅ ተደርገዋል []።

ዋናው ግምት ውስጥ መግባት ያለበት ጉዳይ – ለመፍረድ ከባድ ሊሆን እንኳን ቢችል – አንድ ሰው ቃለ መጠይቅ ለመስጠት በቂ የስነ-ልቦና ደህንነት ይሰማው እንደሆነ ነው። ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ከአሰቃቂ ሁኔታ በኋላ በተለይ ከፍ ያለ የጭንቀት ደረጃ እያጋጠመው ከሆነ፣ ደህነት የማይሰማቸው ሊሆኑ ይችላል። ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት  ብዙ ግዜ ለብቻው የሚከሰት አለመሆኑን አይርሱ – ተጎጂዎች በቅርብ ጊዜ ሌላ ዓይነት ጥቃት የደረሳቸው፣ የቤተሰብ አባላት መጥፋት ወይም መፈናቀል ያጋጠማቸው ሊሆኑ ይችላሉ።

የምንጭዎ እንዲሁም የእራስዎን ስሜታዊ እና አካላዊ ደህንነት ለመገምገም ማሰብ ከባድ ሊሆን ይችላል። መፍትሄው ብዙውን ጊዜ ሰዎች ቃለ መጠይቁ ምን እንደሚመስል እንዲወስኑ እና እንዴት እንደሚካሄድ ላይ የተወሰነ ቁጥጥር እንዲኖራቸው ማድረግ ነው። አብዛኛዎቹ እነዚህ ጉዳዮች ከየፈቃድ ስምምነት ጥያቄ ጋር የተዛመዱ ናቸው – ይህን በተመለከተ ተጨማሪ በክፍል ቀ.3

መገለል እና እንዴት ዘገባው ወደ መጥፎ ነገር ሊያመራ እንደሚችል

ወደ አንድ ሰው መቅረብ ደህንነታቸውን እና ግላዊነትን አደጋ ላይ ይጥላል እንደሆነ ራስዎን ይጠይቁ። በአንዳንድ ማህበረሰቦች ውስጥ፣ ተደፍረዋል ተብሎ መጠርጠራቸው ብቻ ውርደትን፣ መገለልን ከዛም አልፎ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል።

ጋዜጠኞች በመስክ ላይ ስላለው ነባራዊ ሁኔታን ሙሉ ግንዛቤ ካላገኙ ነገሮች እንዴት ሊበላሹ እንደሚችሉ የሚያሳይ ከኢራቅ የተወሰደ ምሳሌ እዚህ ቀርቧል።

ዮሃና ፎስተር እና ሼሪዛን ሚንዋላ በተከታታይ 26 ቃለመጠይቆች በማድረግ የያዚዲ ሴቶች ስለ በአይሲስ (ISIS) እጅ የግዞት፣ መደፈር እና ሕገወጥ የሰዎች ዝውውር ሰለባ በሆኑ ሴቶች እና ልጃገረዶች የተደረገ የሚዲያ ዘገባ ምንነት እና ተፅእኖ ያላቸውን ግንዛቤ ዳስሰዋል። ውጤታቸውን እ.አ.አ በ2018 በወጣ የምርምር ወረቀት ላይ አስቀምጠዋል። የሚከተሉት አንዳንድ ቁልፍ ቀመሮች ይመልከቱ፤

በአለም ላይ እንዳሉት ሌሎች ሴቶች፣ የያዚዲ ሴቶች ከራሳቸው ይልቅ የማህበረሰቡን ፍላጎት እንዲያስቀድሙ የሚጠይቅ የተለመደ የስርዓተ-ፆታ ችግር ገጥሟቸዋል።

በተለይም፣ ምንም እንኳን የራሳቸው አካላዊ፣ ክብር እና ስሜታቸው የመጎዳት አደጋዎች ቢኖሩም አሰቃቂ ታሪኮቻቸውን ለዓለም ለመስጠት መስዋዕትነት ለመክፈል ውሳኔ ገጥሟቸዋል። በእርግጥ የያዚዲ ሴቶች ይህን እንዲያደርጉ በያዚዲ ወንዶች በቀጥታ ተበረታተው ነበር… ምንም እንኳን ክብራቸውን በማጣታቸው እንደማይገለሉ ወይም በቤተሰቦቻቸው እና በማህበረሰባቸው መጥፎ አያያዝ እንደማይደረግላቸው ወይም ተቀባይነት እንደማያጡ እውነተኛ ማረጋገጫዎች ቢኖሩም፣ በተለይም በጊዜ ሂደት።

ቃለ መጠይቅ ከተደረገላቸው የያዚዲ ሴቶች አንዷ እንዲህ ብላለች፡-

“መጀመሪያ ላይ [ከአይሲስ] ስመለስ አንድ ኮሚቴ መቅጃ ይዞ መጥቶ ታሪክሽን እንመዘግባለን ሲለኝ ‘አይሆንም’ ስላልኩኝ ወደ የባሌ ወንድም ሄደው ‘ከኛ ጋር ማውራት እምቢ ብላለች’ ብለው ነገሩት።'”

ተጨማሪ የማስገደድ ደረጃዎችን በማከል፣ የያዚዲ ሴቶች በሚተማመኑባቸው ካምፖች ውስጥ ይኖሩ ነበር፣ እና የሰብአዊ አገልግሎት አቅራቢዎችን፣ የካምፕ ሰራተኞችን እና ጋዜጠኞችን ለማስደሰት ባለው ዕዳ ወይም ግዴታ ተሰምቷቸው ነበር ሁሉም የተረፉት ታሪካቸውን እንዲናገሩ ተጨማሪ ጫና ያደርጉ ነበር።

የያዚዲ ሴቶች በመጠለያዎች ውስጥ በሚኖሩበት ወቅት የሰብአዊ አገልግሎት አቅራቢዎችን፣ የካምፕ ሰራተኞችን እና ጋዜጠኞችን በተጎጂዎቹ ተጨማሪ ጫና ያደርጉ ስለነበር ዕዳ ወይም ግዴታ ተሰምቷቸው እነሱን ለማስደሰት ታሪካቸውን እንዲናገሩ ተጨማሪ አስገዳጅ ሁኔታ ገጥሞዋቸዋል።

“ያዚዲ ሴት በአይሲስ ለሦስት ወራት ያህል የወሲብ ባሪያ ሆና ተይዛ የነበረችና በቡድን የተደፈረች ስለደረሰባት አሰቀያሚ ስቃይ ትናገራለች፣ “የአይሲስ የወሲብ ባሪያ ሴት ልጆችን ‘በትንሽ ሲጋራ’ ሳይቀር ይሸጣሉ” እና “የያዚዲ ሴቶች በዳዒሽ ከተደፈሩ በኋላ ‘ድንግልናን ለመመለስ’ ቀዶ ጥገና ይደረግላቸዋል” የሚሉ የዜናዊ ዘገባ እንደሚከተሉት በመሳሰሉት ስሜት ቀስቃሽ አርዕስተ ዜናዎች ሲወጡ የመገለል እድልን ከፍ አድርጎታል። []

ተጨማሪ መረጃዎች፤ ደህንነት

አደገኛ የስራ ስምሪቶች ላይ ደህንነትን ለመጠበቅ የሚመለከቱ በመገናኛ ብዙሃን ድጋፍ እና ጥበቃ ድርጅቶች በሚታተሙ የተለያዩ መመሪያዎች አሉ። በሲፒጄ (የጋዜጠኞች ጥበቃ ኮሚቴ)፣ ACOS Alliance (የደህንነት ባህል) እና የሮሪ ፔክ ትረስት (ለግል ጋዜጠኞች ተብሎ የተዘጋጀ) አጠቃላይ እይታዎችን በመመልከት እንዲጀምሩ እንመክራለን፣ ነገር ግን ሌሎች ብዙ ጠቃሚ ምንጮችም አሉ። (ከዛም አልፎ እነዚሁ ድርጅቶች ስልጠና ማግኘት እና ሌሎች አይነት ድጋፎችን በተመለከተ ምክር ሊሰጡ ይችላሉ።)

ደህንነት እና ጥበቃ (Safe and Secure) ከ’ዶክ ሶሳይቲ’ ለፊልም ሰሪዎች ተብሎ የተነደፈ ነው። ስለ አካላዊ ደህንነት ጠቃሚ ምክሮችን ከመስጠት በተጨማሪ የቡድን አባላትን እና አስተዋፅዖዎችን ከህጋዊ እና ዲጂታል የደህንነት ስጋቶች ለመጠበቅ ለማንኛውም ጋዜጠኛ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ጠቃሚ ምክር ይሰጣል - ሁለት ብዙውን ጊዜ ችላ የተባሉ ወሳኝ ገጽታዎች። ‘ግሎባል ኢንቬስትጌቲቭ ጋዜጠኝነት ኔትወርክ’ም ይህንን ዝርዝር የመረጃ ድህረገፅ ያቀርባል።

አዘጋጅ ወይም ስራ አስኪያጅ ከሆኑ ድግሞ፣ ለዜና ድርጅቶች የተዘጋጀ ACOS የደህንነት መገምገሚያ መሳሪያ እና የዳርት ማእከል ለአሰቃቂ ሁኔታ ከተጋለጡ ከነፃ ጋዜጠኞች ጋር እንዴት መስራት እንደሚቻል የሚገልጽ መመሪያን ይመልከቱ። የሲፒጄ ባልደረባ የሆነው ፍራንክ ስሚዝ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) በሚዘግቡ ጋዜጠኞች ላይ ስለሚችሉ አደጋዎች የሚመለከት ማብራሪያ ጽፏል።

የግርጌ ማስታወሻዎች፡-

 • ሀ.

  ይመልከቱ፡ https://www.cjr.org/analysis/rohingya-interviews.php

 • ለ.

  ጆሃና ኢ. ፎስተር እና ሸሪዛን ሚንዋላ፣ የያዚዲ ሴቶች ድምጽ፤ ስለጋዜጠኝነት አሰራር ያሉ እይታዎች በአይሲስ የወሲብ ጥቃቶች ዘገባዎች፡ ’ Women’s Studies International Forum 67 (2018): 53–64.