#3.
ሦስት መሰረታዊ ጥያቄዎች

ቃለመጠይቅ የማደርግላቸው ሰዎች በመሳተፋቸው ሊደርስባቸው የሚችል መዘዝ ሙሉ በሙሉ ተረድተዋልን?

አንድ ሰው ምስክርነታቸውን እንድትጠቀሙ ወይም ምስላቸው እንዲነሳ ፈቃደና መሆናቸው ብቻ በቂ አ ይደለም። ሙሉ በሙሉ ግንዛቤ ካላገኙ በስተቀር የፈቃድ ስምምነቱ ትርጉም የለውም።

አንድ ሰው ለመናገር ተስማምቷል ወይም ምስሉን እንዲታይ ፈቅዷል ማለት፣ ምን እንደሚያጠቃልል በትክክል ያውቃል ማለት አይደለም። እርስዎ ምን ማድረግ እንደሚፈልጉ ለአንድ ሰው መንገር በቂ አይደለም። አደጋዎቹን እንዲረዱ እና እውነተኛ ምርጫዎች እንዲኖራቸው ለማድረግ የበለጠ ርቀት መሄድ ይኖርብዎታል። በተለይም ማወቅ ያለባቸው፡-

  • የቃለ መጠይቁ ወይም የቀረጻው ሂደት እንዴት እንደሚሰራ።
  • የትኞቹን ታሪኮች እና ገጽታዎች ለመወያየት እንዳሰባችሁ ነው።
  • መረጃዎችን ማን ማየት እንደሚችል እና ለምን ያህል ጊዜ ሊቆይ እንደሚችል

የፈቃድ ስምምነትን ማግኘት ዕድል እንጂ መወጣት የሚያስፈልገው እንቅፋት አይደለም። ምንጭዎ ስጋቶቹን የሚያውቅ ከሆነ እና ሙሉ በሙሉ ከተስማማ የበለጠ ውጤታማ ቃለ መጠይቅ ያገኛሉ።

የቃለ መጠይቁን የፈቃድ ስምምነት ለማግኘት የተለመደው የጋዜጠኝነት አብነት ዘጋቢዎች፣ ታዋቂ ሰዎች ቃለ መጠይቅ ከሚያደርጉበት ሁኔታ የመነጨ ነው። እነዚህ ግን ብዙውን ጊዜ በለመዱት ጨዋታ ውስጥ የተቀመጡትን ህጎች የሚረዱ ጠንካራ ሰዎች ናቸው። ዋናው ትኩረት ማግኘታቸውን ማረጋገጥ እና ፖለቲከኛውን ወይም ነጋዴውን በተቻለ መጠን ስማቸው በግልጽ ተጠቅሞ እንዲናገሩ ማድረግ ነው።

ከተጋላጭ ሰዎች በሚሰሩበት ግዜ ግን፣ በጋዜጠኛው እና ምንጮች መካከል ያለው የኃይል ሚዛን በግልባጩ ስለሚሆን ያንን ሞዴል መጠቀም ትክክል አይደለም። በተጨማሪም፣ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) በሚከሰቱበት ሁኔታዎች ውስጥ መጀመሪያው ግምት ውስጥ መግባት ያለበት የምንጩን ስም-አልባነት ጥበቃ መሆን አለበት። ይህ ማለት ተጎጂው ሰው በይፋ የመናገር ግዴታ አለበት የሚለውን ግምት ወደ ጎን መተው ማለት ነው።

በመጀመርያ ደረጃ ይህ ግልጽ ነው። እያንዳንዱ ጋዜጠኛ ይህን ያውቃል (ወይንም ማወቅ አለበት)። በሌላ ደረጃ፣ የፖለቲካ ሞዴል ትሩፋት ስር የሰደደ በመሆኑ አሁንም ጋዜጠኞችን ማጥመድ ይችላል። ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ላይ እየዘገቡ ከሆነ፣ ቆም ማለት እና ትርጉም ያለው ስምምነት ተብሎ ሊጠራ ከሚችል ሌላ መነሻ መጀመርዎን ማረጋገጥ እንዳለቦት ማሰብ ይኖርብዎታል፤

  1. በመጀመሪያ፣ በግንዛቤ ላይ የተመሰረተ ስምምነት በዋነኛነት መግቢያ ለማግኘት እና አንድ ሰው ለቃለ መጠይቅ እንዲስማማ ማድረግ ነው የሚለውን ሃሳብ ወደጎን ይተዉ፤ አይደለም። ከፍተኛ አደጋዎች ባለበት ግንኙነት እንዴት አንድ ሰው የበለጠ አስተማማኝ መሰረት ያለው ደህንነት እንደሚገነባ ማሰስ ነው። አንድ ሰው ሀሳቡን ከቀየረ እና መናገር እንደማይፈልግ ግልጽ ከሆነ፣ ያንን እንደ ጥሩ ውጤት ይውሰዱት። ልክ የሙከራ ፈተና ውስጥ እንደሚሆነው፣ ለዚህ ሚና ትክክል አይደሉም ማለት ነው።
  2. ሁለተኛ፣ ስምምነትን ማግኘት የአንድ ጊዜ ተግባር እና፣ ልክ በውይይት መጀመሪያ ላይ የሚከሰት ህጋዊነት ያለው ደንብ አይደለም። ቀጣይነት ያለው ሂደት፣ በልዩ ዝርዝሮች ላይ ወይም በአጠቃላይ ውይይቱ የመዘገብ መብት ለማግኘት ከአንድ ጊዜ በላይ ሊጎበኝ የሚችልበት ድርድር ነው።

አንድን ሰው እንደ ወሲባዊ ጥቃት ያለ የጠበቀ የግል ጉዳይ እንዲናገር በጭራሽ አያስጨንቁ ወይም አያታልሉት። ነፃ እና ግንዛቤ ላይ የተመሠረተ ትክክለኛ ምርጫ መሆን አለበት።

 

ማን የፈቃድ ስምምነት መስጠት ይችላል?

ፈቃድ መስጠት የሚችለው ብቸኛው ሰው ባለጉዳዩ (ተጎጂው) ነው። ግለሰቡ ለአካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ወይም በሆነ መንገድ ሙሉ በሙሉ በመረጃ ላይ የተመሰረተ ፍርድ ለመስጠት የማይችል ሰው ከሆነ፣ ወላጅ ወይም አሳዳጊ ከሆነ ሰው ተጨማሪ ስምምነት ሊያስፈልግ ይችላል።

ነገር ግን በማንኛውም ሁኔታ፣ ከተጠያው ትርጉም ያለው የፈቃድ ስምምነት ካልተሰጠዎት – ፈቃድ የለዎትም። የአንድ ዘመድ፣ የአንድ ሰው ጠበቃ፣ አገናኝ ወይም የተቀባይነት ያለው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት አማላጅ ቃል የፈቃድ ስምምነትን አያመለክትም። ድርድሩ በቀጥታ ከምንጩ ጋር መሆን አለበት።

ከአስተርጓሚ ጋር እየሰሩ ከሆነ፣ ከምንጩ ጋር የሚያደርጉት ውይይት እርስዎ እያደረጉት ያሉት ነው ብለው የሚያስቡትን መሆኑን ማረጋገጥ አለብዎት። ይህ፣ ጋዜጠኛ ጂና ሙር እንደገለጸው ችግር ሊፈጥር ይችላል። ተጨማሪ እርምጃዎችን ሊወስድ ይችላል። ለአስተርጓሚዎ መንገር ያለብዎት፡-

 

“እራሴን በመድገሜ ይቅርታ፣ ነገር ግን አላማዬ ግልፅ መሆኑን ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፤ እኔ ማን እንደሆንኩ እነሆ። እኔ እየሰራሁት ያለሁት ይኸው ነው…” ተርጓሚው “እሱማ አስቀድሜ ጠየቅኳት” ብሎ ከተናገረ እርስዎ “አመሰግናለሁ፣ ግን የስራዬ ደንብ ራሴን በቀጥታ እንድጠይቃት ያስገድደኛል” ብለው “ስለዚህ፣ ካላስቸገርኩህ ይህንን ለመጨረሻ ጊዜ ለማረጋገጥ እንድንችል የምናገረውን ተርጉምልኝ…” ይበሉ።[]

የስልጣን ባለቤትነቱ ግልጽ ባልሆነ ሁኔታ ተጎጂዎች ለእነርሱ ጥቅም በማይሰጥበት ወቅት እንዲናገሩ ግፊት ሊደረግባቸው ይችላል። እንደ ጋዜጠኛ፣ አንድ ሰው እውነተኛ ምርጫን ተጠቅሞ ፈቃድ ለመስጠት ይችላል ብሎ ከመገመትዎ በፊት ሁሉንም የተጋላጭነት ገጽታዎች በጥልቀት የመመርመር ግዴታ አለብዎት።

 

ከጥቃቱ በኋላ ባለው አጭር ግዜ (በተለይ ከደቂቃዎች እና ሰዓታት፣ ምናልባትም ከቀናት በኋላ) ውስጥ ተጎጂው ትርጉም ያለው ስምምነት ለመስጠት በማይችልበት ሁኔታ መሆኑ የሚጠበቅ ነው። የማናቸውም ተጎጂዎች ማንነት መለየት እንደማይቻል እርግጠኛ ከሆኑ፣ ስለሁኔታው የጀርባ መረጃን በመጠቀም የተከሰተውን ነገር የመዘገብ መንገድ ሊኖር ይችላል። ነገር ግን እንደዚህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ያለ አንድ ሰው ስማቸው እንዳይገለጽ መብቱን ለመተው ወይም ላለመስጠት ውሳኔ ለማድረግ እንደማይችል ግልጽ ይሁኑ። ያ ከጥቃቱ የበለጠ ርቀት ያስፈልገዋል።

ከአስተርጓሚዎች ጋር መሥራት

እርስዎ በማይኖሩበት አካባቢ እየሰሩ ከሆነ፣ ቋንቋውን ከሚናገሩ እና የመሬቱን አቀማመጥ ከሚያውቁ የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች እና ተርጓሚዎች ጋር ያለዎት ግንኙነት ወሳኝ ነው። ነገር ግን እነሱ የስሜት-ቀውስ ሁኔታን ንቃት አላቸው ብለው ማሰብ አይችሉም።

የሚተረጉም ሰው የሚከተለውን መረዳቱን ማረጋገጥ አለቦት፡-

  • ርዕሰ ጉዳዩ ስሜትን የሚፈትን ሊሆን ይችላል።
  • በምንጮች ላይ ጫና ማድረግ ወይም እንዲናገሩ ማበረታቻ ማቅረብ የለባቸውም።
  • በግንዛቤ ላይ የተመሰረተ የፈቃድ ስምምነት እና የስሜት-ቀውስን ግምት ውስጥ ያስገባ የቃለ መጠይቅ አቀራረቦችን መጠቀም አለባቸው። (እዚህ መመሪያ ያሉ መረጃዎችን አሳዩዋቸው)
  • ወደ ጭንቀት መግፋት ወይም ያለምክንያት ዝርዝር ምርመራ ማድረግ የለባቸውም።

ቃለ መጠይቅ እንዴት እንደምታደርግ የምትችለውን ያህል አስቀድመህ በዝርዝር ማቀድ አለብህ፣ የምታደርገውን እስከ መለማመድም ሊሆን ይችላል። ስለአደጋዎች እና ስለአካባቢው ባህላዊ ደንቦች ጥልቅ ውይይት ያድርጉ። እርስዎ እንዴት እየሰሩ እንደሆነ እና ለእርስዎ መተርጎም አስቸጋሪ ሆኖባቸው እንደሆነ አስተያየት እንዲሰጡዎት አስተርጓሚዎን ይጠይቁ።በግንኙነትዎ ላይ የበለጠ መተማመን የተሻለ ይሆናል። እንዲሁም በግል እንዴት እንደሆኑ እና በራሳቸው ወይም በቤተሰቦቻቸው ላይ ምንም አይነት አደጋ እንዳይኖር ማረጋገጥ አለብዎት።

 

የፈቃድ ስምምነትን ትርጉም ያለው የሚያደርገው ምንድን ነው?

አንድ ሰው ለመናገር ስለተስማማ፣ ያ ማለት ምን እንደሚያካትት በሚገባ ተረድተዋል ማለት አይደለም።

ስለ ሂደቱ፣ ምን ሊጠይቋቸው እንደሚፈልጉ እና ይህ ምን ያህል ጭንቀት ሊሆን እንደሚችል፣ እና በእነርሱ አስተዋጽዖ ምን ሊፈጠር እንደሚችል ግልጽ ላይሆንላቸው ይችላል። ሀሳቡ፣ የሆነ ወደ ፊት ላይ የበለጠ ጉዳት ሊያደርስ የሚችል ያልተጠበቁ ነገሮችን ማስወገድ ነው። እርስዎ እና ቃለ-መጠይቅ የሚያደርጉት ሰው ስለሚከተሉት ነገሮች ግልጽ መሆናችሁን ያረጋግጡ፡-

  • የውይይቱ አላማ ምን እንደሆነ?
  • ማንን ይሳተፋል?
  • ማውራት የማይፈልጉባቸው ‘የማይነኩዋቸው ነገሮች’ ካሉ።
  • ዘገባው ማን ያየዋል (እና በአለም ላይ በየትኛውም ቦታ በበይነ መረብ በኩል ያለውን ተደራሽነት)።
  • ፊልም ከሆነ፣ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚቆይ እና እንዴት እንደሚከፋፈል
  • ማንነታቸው እንዳይገለጽ እንዴት ይጠበቃል።
  • በኢንተርኔት የጥቃት ሰለባ የሚሆኑበት ዕድል መኖር አለመኖሩን

ምስሎችን የሚጠቀሙ ከሆነ ተጠያቂውን በምስሎች ላይ በሚደረጉ ውሳኔዎች ማሳተፍ እና አለም ስለራሳቸው እና የሚኖሩበት ማህበረሰብ ምን እንደሚያይ ማሳየት ጥሩ ልምምድ ነው። የያዚዲ ሴቶች በአይሲስ መደፈራቸውን የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ሴቶች ፊታቸውን ተከናንበው ፎቶግራፍ በማንሳት ስማቸው እንዳይገለጽ ዋስትና የሰጡ መስሏቸው ነበር። ነገር ግን ሴቲቱ እራሳቸው ከዓይኖቻቸው እና በጣም ከሚለዩት ነጠላ መካከል አንዱ ሌላውን በግልፅ መለየት ይችላል. [#8 ይመልከቱ።]

ጥልቅ፣ ግልጽ ያልሆነ የትጋት ደረጃዎች ሊያስፈልግ ይችላል – ለምሳሌ በእነዚህ በጣም ከባድ ጉዳዮች ግልጽ ካልሆኑ፡-

  • ፊልሙ ወይም የመጨረሻ ዘገባው የወንጀለኞችን ወይም የሚደግፏቸውን ቡድኖች ድምጽ ያካትታልን? ከእውነታው በኋላ ይህንን ማወቁ መረጋጋትን ሊያሳጣ ይችላል። አንድ ተጎጂ ‘መልስ የመስጠት መብት’ የሚለውን መርህ እና እንዴት ማንም ሰው ጥቃት ፈጻሚዎችን ሃሳባቸው እንዲሰጡ ዕድል እንደሚሰጥ በመረዳት ረገድ ትልቅ ችግር ሊኖረው ይችላል። ይህንን ቀደም ብሎ ማብራራት ይሻላል።
  • እርስዎ ያላነሱት የተደበቁ ተስፋዎች አሉ? ቃለ መጠይቅ የተደረገለት እርስዎን በማነጋገራቸው ለህብረተሰቡ ቀጥተኛ እርዳታ እንደሚያመጣ ያምናል? ወይም እርስዎ ሊሰጡት ማይችሉበት ለቀጣይ የስነ-ልቦና ድጋፍ ወይም ጓደኝነት ከእርስዎ ይጠብቃሉ? [ስለዚህ ለበለጠ ቁ.6 ይመልከቱ።]
  • ጋዜጠኞች ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ሰለባ የሆኑ ሰዎች ጋር ስለሚያደርጉት ውይይት ህጋዊ ችግሮች እምብዛም አያስቡም። ምንጫችሁ በፍርድ ቤት ፍትህ ለመፈለግ አላማ ያላቸው ከሆነ፣ ከጋዜጠኞች ጋር መነጋገር ጉዳያቸውን ሊያበላሽ ይችላል። እንዲሁም ሁሉም ሰነዶችዎ ሊገኙ የሚችሉ ማስረጃዎች እንደሆኑ ሊቆጠሩ እንደሚችሉ ማወቅ አለብዎት።

የፍትህ ሂደቱ እና የበርካታ መግለጫዎች አደጋ

ለጥቃት ሰለባዎች ፍትህን የመፈለግ ህጋዊ ሂደት አንዳንድ ጊዜ በበርካታ ቃለመጠይቆች ሊጣስ ይችላል። ኮሎምቢያዊቷ ጋዜጠኛ ጂንት ቤዶያ ሊማ እንደሚከተለው ትገልጸዋለች፡-

በጾታዊ ጥቃት ወቅት ከሚገጥሙን ችግሮች አንዱ ነው።

በኮሎምቢያ ተጎጂዋ ስለ ክስተቶቹ ምስክርነት ከአንድ ጊዜ በላይ የመስጠት ግዴታ እንደሌለባት ህጉ ይናገራል። ነገር ግን ከሞላ ጎደል ሁሉም ተጎጂዎች ስለአንድ አጋጣሚ ከአራት በላይ ምስክርነት እንዲሰጡ ይገደዳሉ እና ይህ በግልጽ የታሪኮች አለመመጣጠን ያስከትላል፤ ይህም ብዙውን ጊዜ የፍትህ ሂደቶች መበላሸት ያስከትላል፣ ተጎጂዋ ለመገናኛ ብዙኀን ምስክርነቷን ስትሰጥ የበለጠ ይባባሳል።

እንደ አለመታደል ሆኖ ጋዜጠኞች ‘እውነተኛውን’ ታሪክ ለማግኘት በምስክሮቹ አለመጣጣም ላይ ይደገፋሉ፤ ነገር ግን ይህ የሚያመነጨው የሂደቶቹ መዘጋት ነው።

በተመሳሳይም ፍርድ ያልተሰጠው የወሲብ ጥቃት የወንጀል ድርጊት የመከላከያ ክርክሮችን ወደ ወንጀለኞቹ እንዲያቀርቡ ያደርጓቸዋል፤ እነዚህም ማስረጃዎቻቸውን በብዙ አጋጣሚዎች ተጎጂዎቹ ከመገናኛ ብዙኀን ጋር በሚያደርጉት በቃለ መጠይቅ መካከል በሚፈጥሩት ‘ተቃርኖ’ ላይ ይመሰረታሉ። ዳኞች የተጎጂው ምስክርነት በካሜራ ፊት የሚቀርብበትን መንገድ፣ ጊዜ፣ ቦታ እና ሁኔታ በጭራሽ አያስቡም። እናም በታሪኩ ላይ የሚያሳድረው ተጽእኖ ከአንድ ጋዜጠኛ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ከስነ-ልቦና ባለሙያ ወይም ከጤና ባለሙያ የተለየ እንደሆነ ግልጽ ነው።

ለጥናታችን አስተዋጽኦ ያደረገችው ጂንት ቤዶያ ሊማ በግንቦት 2000 እና በነሐሴ 2003 በኮሎምቢያ ሁለት ጊዜ ታፍናለች። እ.ኤ.አ. በ 2001 የዓለም አቀፍ የሴቶች ሚዲያ ፋውንዴሽን በጋዜጠኝነት የጀግንነት ሽልማት አግኝታለች።በ2020 ከአለም የጋዜጦች እና የዜና አታሚዎች ማህበር የነፃነት ወርቃማ ብዕር ሽልማት አሸንፋለች።

ተጨማሪ መረጃዎች፡ የፈቃድ ስምምነት

በምስራቅ አፍሪካ የምትኖር አሜሪካዊት ጋዜጠኛ ጂና ሙር ለዚህ ምክክር አበርክታለች።

በእነዚህ ሁለት ጠቃሚ ጽሑፎች ውስጥ የስምምነት ጉዳዮችን በበለጠ ዝርዝር ትዳስሳለች፡ The Pornography Trap in Columbia Journalism Review እና Five Ideas on Meaningful Consent in Trauma Journalism.

የግርጌ ማስታወሻዎች፡-