#4.
አደጋን የማያስከትሉ ሦስት አስፈላጊ አሰራሮች

ተጎጂዎች በራሳቸው መንገድ እና በራሳቸው ጊዜ እንዲናገሩ ፍቀድላቸው

በወሲባዊ ጥቃት ጊዜ ሰዎች በአጥቂዎች እንደ ዕቃ ይቆጠራሉ - በሚደርስባቸው ነገር ላይ ቁጥጥር እንዳላቸው ግለሰቦች አይደሉም የሚቆጠሩት። ያንን ሁኔታ በመለወጥ ተጠያቂዎችን ታሪካቸውን እንዴት እንደሚናገሩ የመወሰን ዕድል መስጠት ይችላሉ?

ለአደጋ የተጋለጡ ሰዎችን ግምት መስጠት፣ በአክብሮት የመያዝ እና ክብራቸውን የመጠበቅ አስፈላጊነት የታወቀ መሆን አለበት። ነገር ግን ይህ በተግባር ላይ ምን ያካትታል?

እንደ ጋዜጠኛ ተጎጂዎችን ቃለ መጠይቅ ሲያደርጉ፣ እርስዎ ላቅ ያለ ቦታ ላይ ነዎት - ምንም ባይሰማውም እንኳ።መተማመን እና የስሜት ደህንነት ልብ ማለት የሚያስፈለጉዋቸው ጉዳዮች ይሆናሉ። ታድያ፣ በጥቂቱም ቢሆን እንደ መቸኮል ወይም ምላሽ እንዲሰጡ መግፋት የመሰሉ ዋናውን በደል የሚያስተጋባ ምንም ነገር አለማድረግ በጣም አስፈላጊ ነው። በአደገኛ ቦታ ላይ እና የጊዜ ገደብ በሚጨናነቁበት ወቅት ላይ ሲሆኑ ይህ በቀላሉ ከግምት ውጭ ሊሆን ይችላል።

ለውይይቱ በቂ ጊዜ ለማቀድ ቅድሚያ ይስጡ እና ተጠያቂውን ማወቃቸው ያረጋግጡ፡-

  • ደስ የማይላቸውን ማንኛውንም ጥያቄዎች መመለስ አያስፈልግም።
  • በማንኛውም ጊዜ ማቆም ምንም ችግር የለውም።
  • እንዳይታተም የሚጠይቁዎትን ማንኛውንም ዝርዝር ማክበር አለብዎት።

በመጀመሪያ ተጠያቂውን እንደ ሰው ይመልከቱ - በሁለተኛ ደረጃ ነው ታሪኩ ለመሰነድ እንደምንጭ መታየት ያለባቸው።

የሚዲያ ቃለ መጠይቅ በዝባዥ ወይም ደህንነቱ ባልተጠበቀ ሁኔታ ከተፈጸመ ተጎጂዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትል ይችላል። ይህ ክፍል አሰቃቂነትን የተገነዘበ ቃለ መጠይቅ ውስጥ ያሉ መሰረታዊ ነገሮችን ያብራራል፤ የሚቀጥለው [ቁ.5] የተወሰኑ የስሜት-ቀውስነት ምላሾችን እና ከተጎጂዎች ጋር በሚሰሩበት ጊዜ ሊያጋጥሟቸው የሚችሉትን ተግዳሮቶች በበለጠ ዝርዝር ይመለከታል።

ብዙ ጊዜ ጋዜጠኞች፣ እንደ ጾታዊ ጥቃት ወይም ማሰቃየት የመሰሉ አስደንጋጭ እና አሳማሚ ታሪኮችን ማውራት ብቻ ሰለባውን ሊጎዳ እንደሚችል መጨነቃቸው የሚገርም አይደለም። ባይነገሩ የሚሻሉ ነገሮችን እንደገና እያነሱ ነው ብለው ይፈሩ ይሆናል። ወይም እንደ ሰው ታሪካቸውን ሲናገሩ የሚያጋጥመውን ጭንቀት አዲስ ጉዳት ከማድረስ ጋር ያመሳስሉት ይሆናል።

ከፆታዊ ጥቃት ተጎጂዎ ጋር የሚሰሩ አብዛኛዎቹ የስሜት-ቀውስን ለባለሞያዎች መናገር ራሱ ትልቅ አደጋዎች ያሉበት እንደሆነ አያስቡም። ቃለ-መጠይቅ የሚደረግለት ሰው በንግግሩ ወቅት ምን ያህል ደህንነት እንደሚሰማው፣ ስለሚያወራው ምን ያህል እንደሚቆጣጠሩ እና እንዲሁም ታሪካቸው በኋላ እንዴት እንደሚታተም በሚሉ ጥያቄዎች ስለሚመረኮዝ ነው[ቁ.7 እና ቀ.8 ይመልከቱ]። ሰዎች እንደተፈረደባቸው ሲሰማቸው ወይም እንዳልሰሙ ሲሰማቸው ወይም ላልሆነ ዓላማ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ ሲሰማቸው፣ ጉዳቱ ሊከሰት ይችላል። በአሰቃቂነት ዙርያ በሚደረጉ ቃለመጠይቆች ውስጥ፣ መተማመን ስስ እና በቀላሉ የሚበላሽ ነገር ነው።

ማውራት በራሱ ከመዘዝ ነፃ ነው ከሚለው ሀሳብ የሚቃረኑ ልዩ ሁኔታዎች አሉ። ለምሳሌ፣ አንድ ሰው ከዚህ በፊት የሸሸገው እና ከዚህ በፊት ያልተመረመረ ከባድ አሰቃቂ ነገር ካጋጠመው፣ ለምሳሌ በልጆች ላይ የሚፈጸም ወሲባዊ ጥቃት፣ መናገር በራሱ አለመረጋጋትን ሊፈጥር እና የተለያዩ አደጋዎችን ሊያስከትል ይችላል። በአጠቃላይ ያልተጠበቁ መረጃዎችን ከማቅረብ ይጠንቀቁ።

ሂደቱን እንዴት ከብዝበዛ ይልቅ የትብብር ማድረግ እንደሚቻል

ለተጎጂዎች ፆታዊ ጥቃት እንደ መሠረታዊ የቁጥጥር መጥፋት ነው – የሆነ የደረሰባቸውን ነገር ለመከላከል አቅመ ቢስ የሆነባቸው። ይህንን ለመቃወም አንዱ መንገድ እንደ ጋዜጠኛ ያለዎትን አንዳንድ የመቆጣጠር ኃይል መስጠት እና በሂደቱ ላይ በሚደረጉ ውሳኔዎች ላይ እንደሚሳተፉ ማድረግ ነው። ትናንሽ ምርጫዎች እንኳን ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ።

በውይይት ውስጥ ማንኛውንም ዝርዝር ከመግባትዎ በፊት የሚከተሉትን ማድረግ አለብዎት፡-

  • መናገር ከባድ ሊሆን እንደሚችል ይግለጹላቸው።
  • የት ቃለ መጠይቅ እንዲሚደረግላቸው እንደሚፈልጉ ለመወሰን ሙሉ ለሙሉ ያሳትፏቸው።
  • ለንግግሩ ብዙ ጉልበት የሚኖራቸው መቼ እና ለምን ያህል ጊዜ ማውራት እንደሚፈልጉ – የትኛው ሰዓት እንደሚስማማቸው ይጠይቁ?
  • በክፍሉ ውስጥ ከእነሱ ጋር መሆን የሚፈልጓቸው እንደ ጓደኛ ወይም ዘመድ ያለ ሰው ካለ ይጠይቁ።
  • ሊናገሩበት የማይፈልጉት ነገር ካለ ጠይቋቸው።
  • ደስ የማይላቸው ማንኛውንም ነገር መመለስ እንደሌለባቸው አረጋግጡላቸው።

ወደ ንግግሩ ከመግባትዎ በፊት እንደ ቃለ-መጠይቅ አድራጊ፣ ሰዎችን ለረዥም ግዜ መናገራቸው እና እረፍት እንደሚያስፈልጋቸው እንዴት እንደሚገነዘቡ ከወዲሁ ማስረዳት ጥሩ ነው። ሰዎች ታሪካቸውን በሚናገሩበት በመሃል ከመጠን በላይ ሊገቡ ይችላሉ። እና በተጨማሪ፣ አብዛኞቻችን ጥያቄዎችን የሚጠይቅን ሰው ለማስደሰት፣ ለመቀጠል ከፍተኛ ፍላጎት ያጋጥመናል። ሲደክማቸው ወይም ውይይቱ ወደ ደስ የማይላቸው አቅጣጫ በሚሄድበት እና ከአቅማቸው በላይ እንደተናገሩ ምልክት ላያሳዩ ይችላሉ። ቃለ መጠይቁ ከመድረሱ በፊት ይህንን ማንሳት – እና ምናልባት በአንድ የተወሰነ ምልክት ላይ መስማማት – እረፍቶችን የሚጠቁሙ ወይም አቅጣጫው ወደ ደህንነቱ የተጠበቀ ርዕስ መቀየር የበለጠ ቀላልና እና ብዙም የማይረብሽ ያደርገዋል።

በሚጠቀሙባቸው ቃላት ላይ መስማማት

ክፍል ቁ.7 በሚታተምበት ጊዜ ስለቋንቋ ምርጫዎች የበለጠ ይናገራል። በቃለ መጠይቁ ወቅት፣ ተጎጂውን የሚስማማቸውን ቃላት እየተጠቀሙ መሆንዎን ያረጋግጡ። የአካባቢ ፈሊጦች እዚህ ጠቃሚ ሊሆኑም ላይሆኑም ይችላሉ። አንዳንድ ግልጽ ደንቦች አሉ። ለምሳሌ ወንጀለኛን እንደ የተጎጂውን ፍቅረኛ መግለጽ ፈጽሞ ተገቢ አይደለም።

አብዛኛዎቹ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሰዎች እራሳቸውን እንደ ‘ተጎጂዎች’ ይገልጻሉ፣ ነገር ግን አንዳንዶች ‘ሰለባ’ የበለጠ ትክክለኛ ቃል እንደሆነ ሊሰማቸው ይችላል እና ሌሎች ደግሞ ሁለቱንም ለማስወገድ ይፈልጉ ይሆናል።በየትኞቹ ቃላቶች ላይ ጥርጣሬ ካለዎት፣ ከጠያቂዎ ጋር ያረጋግጡ እና ምን እንደሚመርጡ ይጠይቁ። በአጠቃላይ፣ ሰዎች እራሳቸውን እንዴት እንደሚለዩ ማክበር ሁልጊዜ አስፈላጊ ነው።

የመስማት ችሎታ

ሰዎች እንደተሰሙ ሲያምኑ፣ የበለጠ የደህንነት ስሜት ይሰማቸዋል እና ከዚያም ሃሳባቸውን በብቃት መሰብሰብ ይችላሉ። በደንብ ማዳመጥ እንደሚቻል ማወቅ ጋዜጠኛ ተጎጂዎች ወደ ውይይት ለማምጣት የሚያስፈልገው ብቸኛው በጣም አስፈላጊ ክህሎት ነው። ለርዕሰ ጉዳይ ቦታ መስጠት እና ቀላል እና በአንጻራዊነት ክፍት የሆኑ፣ ሰዎችን እንዴት እንደሚመልሱ ምርጫ የሚሰጡ ጥያቄዎችን መጠየቅን ይጨምራል። ምርጫው ግን ከመጠን በላይ እንዳይሆን ይመረጣል።

ያስታውሱ፣ በክፍል #2 እንደተብራራው፣ ፈቃድን ማረጋገጥ ቀጣይ ሂደት እንጂ የአንድ ጊዜ ክስተት አይደለም።ጥያቄውን ከማቅረብዎ በፊት፣ “ስለ… (አንድ የተወሰነ ርዕስ ወይም ክስተት) ብጠይቅዎት ችግር አለው?” በማለት ሊጠይቁት ይችላሉ። ከዚያ ሰዎች በነፃነት ምላሽ እንዲሰጡ ይፍቀዱ። በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሌሎች ቦታዎች ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ተጎጂዎች ጋር የምትሰራው ኬቲ ሮብጃንት ለጋዜጠኞች ልዩ የሆነ ምክር አላት፡-

ስለ አጠቃላይ ክስተቶች ክፍት የሆኑ ጥያቄዎችን ከመጠየቅ ይልቅ፣ ምንጩን ሊናገሩት የሚፈልጉትን ልዩ ነገር እንዳለ አስቀድመው ይግለጹ። ከዚያ ስለዚያ ክስተት ወይም ርዕስ የቻሉትን ያህል እንዲነግሩዎት ይጠይቋቸው። ለማጋራት ምቾት የሚሰማቸውን ሁሉንም መረጃዎች ከሰጡዎት በኋላ ጉልህ የሆኑትን ክፍሎች ማውጣት የእርስዎ ስራ ይሆናል። ይህ ማጋራት ወይም ማሰብ የማይፈልጉትን ዝርዝሮች እንዲናገር ማስገደድን ማስወገድ የሚቻልበት አንዱ መንገድ ነው።[]

የውጤታማ ማዳመጥ ጠቋሚዎች የሚከተሉትን ያካትታሉ፡-

  • ዝምታን መፍቀድ እና ሰዎች ሀሳባቸውን እንዲሰበስቡ ቦታ መስጠት።
  • እየተከታተሉ መሆንዎን ለማሳየት በቃልም ወይም፣ እየቀረጹ ከሆነ፣ የቃል ያልሆኑ ምልክቶችን ይጠቀሙ።
  • ቁልፍ ነጥቦችን መረዳትዎን ለማረጋገጥ ተመልሰው መፈተሽ።
  • ከተናጋሪው ትኩረትን እንዳይወስዱ ከራስዎ ምቾት ማጣት ጋር እንዴት በትዕግስት ቁጭ ማለት እንደሚችሉ ማወቅ።

እነዚህን ማስወገድ ይሞክሩ፡-

  • የሰዎችን ዓረፍተ ነገር ለእነሱ መጨረስ ወይም የሃሳባቸውን ሰንሰለት በድንገት መቁረጥ (በማስታወስ ውስጥ ካልጠፉ በስተቀር – ክፍል # 5 ይመልከቱ)።
  • ማንኛውንም የፍርድ ስሜት መስጠት – ለምሳሌ፣ አንድ ሰው የሚያስደነግጥ ነገር ሲያወራ የተደናገጠ ፊት ማሳየት (ምን ያህል እንዳሳሰባቸው ወይም እንዳዘኑ መግለጽ ደህና ነው።)
  • ማንኛውም ተገቢ ያልሆነ አካላዊ ዝርዝሮች ለማግኘት ግፊት ማድረግ።
  • ለሰዎች ምን እንደሚሰማቸው እንደሚያውቁ መንገር (ሰዎች እርስዎን ማመን አይችሉም)።

እንዲሁም ተመሳሳይ ክስተቶች እንዳጋጠሙዎት ለሰዎች በመንገር ወይም ወደ የግል ታሪክ ዝርዝር ውስጥ ላለመግባት መጠንቀቅ አለብዎት።

በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ይህ መተማመንን ሊፈጥር እና ውይይቱን ሊያዳብር ይችላል፣ በሌሎች ውስጥ፣ ከተናጋው ትኩረቱን ሊወስድ ይችላል እና ለእነርሱ ያጋጠማቸው ተሞክሮ እየቀነሱ ወይም ወደ ጎን እየገፉ እንደሆነ እንዲሰማቸው ያደርጋል። (ጤናማ ወሰንን የመጠበቅ አስፈላጊነት በክፍል ቁ.6 የበለጠ ተብራርቷል።)

ጊዜን መቆጣጠር እና በጥሩ ሁኔታ ማብቃት

የዚህ ክፍል ርዕስ፣ ተጎጂዎችን በራሳቸው መንገድ እና በራሳቸው ጊዜ እንዲናገሩ ቦታ መፍቀድ ማለት ግን ጊዜን በመቆጣጠር ረገድ ሙሉ በሙሉ ቸልተኛ መሆን አለብዎት ማለት አይደለም። ሰዎች ለአደጋ የተጋለጡ ሲሆኑ ውይይቱ አንዳንድ መመሪያዎችን ቢኖራቸው ይጠቀማሉ። እንዲሁም ከላይ እንደተጠቀሰው የተጽዕኖ ደረጃቸውን መከታተል ያስፈልግዎታል። (በአካባቢው ውስጥ የሚቆዩ ከሆነ፣ ሁል ጊዜ ተመልሰው መጥተው ውይይቱን ሊቀጥሉ እንደሚችሉ ሃሳብ ማቅረብ ይችላሉ።)

አንዳንድ የሕክምና ባለሙያዎች ስለ ‘ሦስት ሦስተኛው’ ደንብ ይናገራሉ።

በሐሳብ ደረጃ የውይይቱ የመጀመሪያ አንድ ሦስተኛው ተናሪው በአንፃራዊነት ደህንነቱ በተሰማው ጊዜ እና ልምዶች ላይ ማተኮር አለበት። መካከለኛው ክፍል፣ ለምሳሌ አስደንጋጭ ክስተቶች፣ በጣም አስቸጋሪ በሆነው ነገሮች ላይ ያተኩራል። የመጨረሻው ክፍል ደግሞ፣ በአሁን እና በወደፊቱ ላይ – ተጎጂውን ወደ እዚህ እና አሁን እንዲመለስ እንደ ድልድይ የሚረዳ ማንኛውም ነገር ይሆናል። ግለሰቡን በቃለ መጠይቁ መጨረሻ ላይ በደረሰበት በጣም መጥፎ ነገር ውስጥ ተዘፍቆ መተው የለብዎትም።

በአዎንታዊ ሁኔታ ለመጨረስ ይሞክሩ፤ ነገር ግን ከመጠን በላይ አያድርጉት፣ እንዲሁም ነገሮች ከእውነታው የተሻሉ እንደሆኑ ያስመስሉ። ሰዎች ይህን ለመቋቋም ምን ጠቃሚ ሆኖ እንዳገኙት እና ለሌሎች ምን እንደሚመክሩ መጠየቅ ይችላሉ። ጠንካራ የመጨረሻ ነጥብ ማግኘት ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። ቢያንስ ሰዎች በቀሪው የቀኑ ሰዓት ምን እንደሚያደርጉ ሁልጊዜ መጠየቅ ይችላሉ። እርግጥ ነው፣ ሰዎችን ማመስገን አይርሱ፣ እና ከወደፊቱ ግንኙነት፣ ስለ ጽሑፉ መረጃ በመላክ እና በመሳሰሉት ጉዳዮች የገቡትን ማንኛውንም ቃል ይጠብቁ።

]የግርጌ ማስታወሻዎች፡-