#5.
አደጋን የማያስከትሉ ሦስት አስፈላጊ አሰራሮች

አሰቃቂነት በትውስታና እና የደህንነት ስሜት ላይ ያለው የማያቋርጥ ተጽእኖ ይረዱ

ከአሰቃቂነትን የተያያዙ ምላሾች አንዳንድ መሰረታዊ እውቀት መኖር ፈታኝ የሆኑ የቃለ መጠይቅ ሁኔታዎችን ለመወጣት እና መዘዝ የሚያስከትሉትን የዘገባ ስህተቶችን ለማስወገድ ይረዳዎታል።

አስጨናቂ ክስተቶችን እንደገና ሲጎበኙ ሰዎች ሊበሳጩ ይችላሉ። ጭንቀት በራሱ ሰዎች ለመናገር ጥሩ ቦታ ላይ አይደሉም ማለት አይደለም። ነገር ግን አንዳንድ ምላሾች ሰዎች በንግግሩ ውስጥ ደህንነት እንደማይሰማቸው ሊያመለክቱ ይችላሉ። ሊያቋርጡ፣ በሩን ለማግኘት ሊያፈላልጉ ወይም በጥቃቱ ጊዜ ያጋጠማቸው ዓይነት አካላዊ ግብረመልስ ሊያሳዩ ይችላሉ።

የስሜት ቀውስ ውስብስብ የባዮ-ሳይኮ-ማህበራዊ ልምድ ነው፤ ጭንቀት በጭራሽ አንድ ነገር ብቻ አይደለም - የተለያዩ ክፍሎች ድብልቅ ነው። የሚዲያ ባለሙያ እንደመሆንዎ መጠን የአዕምሮ ሳይንስን ማወቅ አያስፈልገዎትም ነገር ግን አንዳንድ መሰረታዊ፣ የመግቢያ ግንዛቤ መኖር የተሻሉ ውሳኔዎችን ለማድረግ ይረዳዎታል፡-

 • ቃለ መጠይቅ የተደረገለት ሰው በምን ሁኔታ እንዳለ እና መቼ ከማውራት እረፍት ሊያስፈልገው እንደሚችል።
 • እንደ ጥፋተኝነት እና እፍረት ባሉት አስቸጋሪ ስሜቶች ላይ ነዳጅ እንዲጨምሩ የሚያደርግ መርማሪ የሚያስመስልዎት የጥያቄ ዘይቤዎችን እንዴት ማስወገድ እንደሚቻል።
 • እስከምን ድረስ አንድ ሰው ስለ አንድ አስደንጋጭ ክስተት ያለው ትውስታ ትክክለኛነት እና ለምን በእነርሱ የትውስታ ክፍተት ውስጥ ማስገባት እንደሌለብዎት ላይ መታመን ምክንያታዊ ነው።

አስገድዶ መድፈር ማንኛውም ሰው ሊደርስበት ከሚችለው እጅግ በጣም አሰቃቂ ገጠመኞች አንዱ ነው። ተጎጂዎች ላጋጠማቸው ቃላት ለማግኘት የሚቸገሩባቸው ብዙ ምክንያቶች አሉ።

ታሪካቸው የሰሙ ሌሎች ሰዎች ምን ይላሉ በማለት የሚከሰት ማፈር እና መፍራት የሰዎችን የንግግር ችሎታ ለመዝጋት ትልቅ ምክንያት ሊሆን ይችላል። በተጨማሪ፣ ስለአሰቃቂ ሁኔታ ማውራት ሰዎች ለመናገር በጣም የሚያሠቃዩ እና የሚያደክሙ ስሜቶችን ሊያመጣ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ ዝምታ ጥሩ ምላሽ ነው። ነገር ግን ብዙውን ጊዜ የነገሮችን ቃላቶች የሰው ልጅ የማስታወስ ችሎታ በአሰቃቂ ሁኔታዎች ውስጥ እንዴት እንደሚሰራ ጋር በተገናኘ ለተለየ ምክንያት ከባድ ሊሆን ይችላል።

ጥቃት ሲደርስብን ወደ የመዳን ሁኔታ እንሄዳለን። ትውስታዎች አሁንም ተመዝግበዋል – ብዙ ጊዜ ግልፅ ባለ መልኩ – ነገር ግን አእምሮው በተለምዶ በሚያሰማራቸው የስርዓት መርሆዎች መሰረት አጣርቶ አያስወግዳቸውም (ይልቁንም ለበለጠ መሰረታዊ የመዳን ስርዓቶች ቅድሚያ ይሰጣል)። ወሲባዊ ጥቃት በደረሰባቸው ሰዎች የተቆራረጠ እና የተበታተነ የማስታወስ ችግር መኖሩ የተለመደ ነው። በጊዜ ቅደም ተከተል ላይ ግንዛቤ የመስጠት ችግር ያለባቸው ክፍተቶች ወይም አለመጣጣሞች ሊኖሩ ይችላሉ። አንዳንድ ነገሮች በልዩ ኃይል ሊመለሱ ይችላሉ፤ ሌሎች ባዶ ሊሆኑ ይችላሉ ወይም በመጀመሪያ በትውስታ ውስጥ ያልተቀመጡ ሊሆኑ ይችላሉ። []

ለእርስዎ እንደ ጋዜጠኛ በተግባራዊ መልኩ ይህ ማለት፡-

 • ተጎጂው ስለአጋጠመው ነገር ፍጹም ወጥነት ያለው ወይም ምክንያታዊ ዘገባ እንዲሰጥዎ መጠበቅ የለብዎትም። አለመመጣጠን የማታለል ዓላማን የሚያሳይ ማስረጃ አይደለም።
 • የእርስዎ ምንጭ ማናቸውንም የታሪኩን ልዩነቶችን ያጸዳሉ ብሎ መጠበቅ ፍትሃዊ አይደለም – ላይችሉ ስለሚችሉ። ትክክለኛ ቅድመ-ተከተሉ አስፈላጊ ከሆነ፣ ሌሎች ክስተቶችን የሚያረጋግጡ መንገዶችን ይፈልጉ።
 • ወደ ኋላ መዞር እና ቀላል የማብራሪያ ጥያቄ መጠየቅ ቀለል ባለ መንገድ ከቀረበ ጥሩ ነው። ነገር ግን በአንድ ሰው ትውስታ ውስጥ ክፍተት ወይም እንቅፋት ካጋጠመዎ በግፊት መረጃ ለማግኘት አይሞክሩ። ያ ከአቅም በላይ በሆነ መንገድ አንድ ነገር ሊያጎድል ይችላል [ከዚህ በታች ያለውን ሣጥን ተመልከት]።
 • አብረዋቸው እየሰሩ ያሉ ሌሎች ሰዎች – ለምሳሌ አዘጋጆችና አራሚዎች – እነዚህን ገደቦችም ማወቅ አለባቸው።

ለጭንቀት ምላሽ መስጠት

ጭንቀት እኛ በምንጠብቀው መንገድ አይታይም። ስሜታዊ ያልሆኑ የሚመስሉ እና በጣም አስከፊ ስለሆኑት ነገሮች ወጥ በሆነ ድምጽ የሚያወሩ ሰዎችን ወይም በማይሆን ቦታዎች ላይ በመሳቅ ውጥረትን የሚለቁ ወይም ትንሽ ወጣ ያሉ የሚመስልዎት ሊያጋጥሙዎት ይችላሉ። እነዚህ ሁሉ ተፈጥሮአዊ፣ በደንብ የተመዘገቡ ግለሰቦች ከአሰቃቂ ሁኔታ በኋላ የሚኖራቸው የሚያሳዩት ምላሽ ነው። የሚያገኟቸውን እያንዳንዱን ሰው በክፍት አእምሮ ይያዙ እና ትክክለኛ የመልስ አሰጣጥ መንገድ አለ ብለው እንዳያስቡ ይጠንቀቁ።

ሰዎች ስላለፈው ነገር ሲናገሩ፣ በተጠቁባቸው ጊዜ (ወይም ጊዜያት) የነበራቸውን ተመሳሳይ ስሜቶች እና አካላዊ ትውስታ እንደገና ሊሰማቸው ይችላል። ይህ መለስተኛ እና በቀላሉ የማይታወቅ ወይም ከባድ በመሆኑ የተነሳ ሰዎችን ከአሁን በኋላ እነዚያን ስሜቶች እንዲታገሡ ከአቅማቸው በላይ የሚገፋ ሊሆን ይችላል።

አንድ ሰው ጠንከር ያለ ምላሽ ካሳየ – ለምሳሌ በከፍተኛ ሁኔታ ይናደዳል፣ ማልቀስ ይጀምራል ወዘተ – ማንኛውንም ነገር ለማድረግ ከመቸኮልዎ በፊት ነገሮችን በራስዎ ውሳኔ ቀነስ ያድርጉ። ካሜራውን በችኮላ ማጥፋት ወይም ቃለ መጠይቁን ማቋረጥ አንድን ሰው እንደዚህ አይነት ስሜት መኖሩ ስህተት እንደሆነ በመግለጽ ሳያስበው ሊያሳፍር ይችላል። አካላዊ ንክኪን ስለመጠቀም ይጠንቀቁ። ያ በተለይ ያልተጠበቀ ከሆነ አስጊ እና አለመረጋጋትን ሊያስከትል ይችላል። በምትኩ፣ የሚከተሉትን ማድረግ ይችላሉ፡-

 • የመረጋጋት ማሳያ መፍጠር
 • የሆነውን ነገር በእነርሱ ላይ መድረሱ እንደሚያሳዝንዎት ይግለጹላቸው።
 • እዚህ ክፍል ሰዎች ከእርስዎ ጋር ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ያስታውሷቸው – አሁን እየሆነ እንዳልሆነ ያረጋግጡላቸው።
 • በዚህ ጊዜ ምን ሊረዳቸው እንደሚችል ጠይቃቸው። ከቃለ መጠይቁ እረፍት ይፈልጋሉ? ብዙውን ጊዜ እንደዚህ ዓይነት ስሜት ሲሰማቸው ምን ያደርጋሉ?

አንድ ሰው በትዝታ ውስጥ ሲጠፋ

በአእምሮ መራቅ በወሲባዊ ጥቃት ጊዜ የሚገለጽ የተለመደ የመዳን ምላሽ ነው። ሁኔታው አስጨናቂ ሲሆን እና ምንም እውነተኛ የማምለጫ መንገድ ከሌለ አንጎል በድንገት ቅጽበታዊ ጥሪ በማድረግ ነገሮችን ለመዝጋት እና ጥቃቱ በትክክል እንዳልተከሰተ አስመስሎ እንዲለይ ያስችለዋል።

ስለደረሰባቸው እንደገና መናገር ሰዎች ጥቃቱ መልሶ እየተከሰተ እንደሆነ እንዲሰማቸው ሊያደርግ ይችላል። አንድ ሰው የደህንነት ስሜት ሲሰማው እና በአእምሮው ሲርቅ ማወቅ ሁልጊዜ ቀላል አይደለም። ሆኖም ግን ሰዎች የሚከተሉትን ሊጀምሩ ይችላሉ፡-

 • ትኩረትን ማጣት፣ እንቅልፍ የያዛቸው ይመስላሉ ወይም ለጥያቄዎች መልስ መስጠት ያቆማሉ።
 • ስለ ሙቀት ስሜት ቅሬታ ማሰማት ወይም በድንገት መላብ ይጀምራሉ።
 • ስለ ራስ ምታት ወይም የአካል ህመም ቅሬታ ማሰማት።
 • ለመውጣት ክፍሉን መቃኘት።

በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሌሎች ቦታዎች ከስደተኞች እና ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ከደረሰባቸው ተጎጂዎች ጋር የምትሰራው ኬቲ ሮብጃንት ይህ ከተፈጠረ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ለጋዜጠኞች ይህንን ምክር ትሰጣለች፡-

ተግባሮችዎን ሊገመቱ የሚችሉ ያድርጓቸው …ምንጊዜም ፈቃድ መጠየቅ ወይም ቀጥሎ ምን ማድረግ እንዳለብዎት ለግለሰቡ ማሳወቅ ጥሩ ነው። በጣም ጥሩው ነገር እነሱን ወደ ሌላ አቅጣጫ ለመቀየር በፍጥነት መሞከር ነው። ንግግርዎን ይቀጥሉ። ስለ እዚህ እና አሁን ያሉ ነገሮችን ይጠይቁ፣ ለምሳሌ፣ “የት እንዳለህ ልትነግረኝ ትችላለህ? ክፍሉ ምን እንደሚመስል መግለፅ ትችላለህ? እነዚያ አይነት ጥያቄዎች እንደ “ደህና ነህ?” ከመሳሰሉት አጠቃላይ ጥያቄዎች የበለጠ አጋዥ ይሆናሉ። []

እፍረት እና እምነት

ስለ ወሲባዊ ጥቃት በሚደረግ ንግግር ውስጥ ለጠንካራ የኀፍረት እና የጥፋተኝነት ስሜት እንዲፈጠር ምን ያህል ቀላል እንደሆነ መረዳት አስፈላጊ ነው። ይህ በድንገት ሊከሰት እና በማንኛውም ጊዜ ከየንግግር ርእሱ ጋር ተመጣጣኝ ያልሆነ መስሎ ሊታይ ይችላል። ሰዎች ለደረሱባቸውና ጥፋታቸው ሊሆን በማይችሉ ነገሮች ራሳቸውን መወንጀል ያልተለመደ ነገር አይደለም።

እና ይህ ስለ ጾታዊ ጥቃት ስነ ልቦና ብቻ አይደለም – የተደፈሩ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ከማያምኑዋቸው፡ የደረሰባቸውን ዝቅ ከሚያደርጉ ወይም ራሳቸው ጥፋተኛ እንደሆኑ ከወነጀሏቸው ቤተሰብ እና የማህበረሰቡ አባላት ጋር መታገል ይኖርባቸዋል።

ስለዚህ ጉዳተኛው እንደማታምኑ ወይም በእነሱ ላይ ለደረሰው ነገር በማንኛውም መንገድ ተጠያቂ እንደሆኑ የሚጠቁም ማንኛውንም ቋንቋ ከመጠቀም ይጠንቀቁ። በዚህ ምክንያት፣ “ለምን” የሚሉ ጥያቄዎች አደገኛ ሊሆኑ ይችላሉ። መርማሪዎች ይወዷቸዋል ምክንያቱም ለመመለስ አስቸጋሪ ስለሆኑ እና የጥፋተኛ እንደምታ ስለሚያሳዩ። ለምሳሌ፣ አንድን ሰው፣ “በዚያን ጊዜ ለምን እዚያ ነበርክ?” ብሎ መጠየቅ፣ መጀመሪያ ላይ እዚያ መሆን እንደሌለባቸው ያስመስላል።

ስለ ስሜቶች መረጃ የሚሹ ጥያቄዎች፣ ለምሳሌ “…ሲያደርጉ ምን ተሰማዎት?” ለተወሳሰቡ እና ተለዋዋጭ ስሜቶች ሊያድሱ እና ነዳጅ ሊጨምሩ ስለሚችሉ በተቻለ ሁኔታ መወገድ አለባቸው።

እና ቀደም ሲል እንደተብራራው፣ ስለተፈጠረው ነገር ተገቢ ያልሆኑ ወይም አካላዊ ዝርዝሮች ላይ የሚያተኩሩ መርማሪ ጥያቄዎችን ከመጠየቅ ይቆጠቡ።

ተጎጂው እውነት እንዳልሆነ በምታውቀው ነገር ካመነ ወይም ያለመስማማት ቢፈጠር እና እነሱን መገዳደር ከፈለግክ ይህን ለማድረግ ትክክለኛው ሰው እንደሆኑ እና ምን ጥቅም እንደሚያስገኝ ራስዎን ይጠይቁ። አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ለመቀበል ከአቅማቸው በላይ የሆነ የደረሱባቸውን ነገሮች አንዱ ለመከላከል ሲሉ አንዳንድ እምነቶችን ሊደገፉ ይችላሉ።

]የግርጌ ማስታወሻዎች፡-