ይህ ለምን?

ይህ መመሪያ መነሻውን ያደረገው በግጭት በተጎዱ አገራት ከወሲባዊ ጥቃት እና ከስቃይ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ዘገባዎችን በመስራት የካበተ ልምድ ያላቸው ጋዜጠኞች እና ፊልም ሰሪዎች ጋር በተደረገ ተደጋጋሚ ውይይት ነው።

በዚህ ስራ ላይ የተሳተፉ በአጠቃላይ በጎ አስተዋጽኦ ለማበርከት ከፍተኛ ፍላጎት አላቸው። ነገር ግን ሁላችንም አንድ ቦታ ላይ  ቆም ብለን ታሪካቸውን ለመንገር የምንፈልጋቸው ሰዎች ላይ በሚኖረን ተራክቦ ተጨማሪ ጉዳት አድርሰን ይሆን ስንል ጠይቀናል።

በግችት ውስት የወሲብ ጥቃት የደረሰባቸውን ግለሰቦች ቃለ መተየቅ ለማድረግ ቀዳሚዎቹ የመገናኛ ብዙለን ባልደረቦች ቢሆኑም
ስልጠናና ድጋፍ የሚያገኙት ግን አልፎ አልፎ ነው።

ይኹን እንጂ ስልጠናና እና ድጋፍ ለማግነት ግን ፍላጎት አለ። ይህ መመሪያ፤ በሲአርኤስቪ ላይ ለመስራት ፍላጎት ያለው ጋዜጠኛም ሆነ የፊልም ባለሙያ  ሊረዳው በሚችል፣ ስምንት ቁልፍ የክህሎት ክፍሎች መድቦታል። እነዚህ ስምንት ክፍሎች የተቀረፁት በጥልቀት እንዲነበቡ እንዲሁም በቀላሉ ለመከለስ እና ለባልደረባ ማጋራት እንዲቻል ተደርገው ነው። በተጨማሪም ተግባራዊ እንዲሆኑ እና መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ ታስቧል።

ይህ ለመገናኛ ብዙኀን ባልደረቦች በጋዜጠኞች የተዘጋጀው መመሪያ፣ ተከታታይ እና ሰፊ ከሆነ ውይይት በኋላ የተጻፈ ነው።

ይህንን መመሪያ በማዘጋጀት ሂደት ውስጥ የሲአርኤስቪ ተጠቂዎችን (የተወሰኑት አሁን የመብት አቀንቃኞች እንዲሁም በጉዳዩ ላይ ባለሙያዎች ናቸው) ፣ የስሜት ቀውስን የሚያክሙ ባለሙያዎች፣ የማህበረሰብ ሰራተኞች እና ጠበቆችን እንዲሁም የፎቶግራፍ ባለሙያዎች፣ ፊልም ባለሙያዎች እና ከፍተኛ አዘጋጆችን አማክረናል።

ይህ ጉዳይ ወሰብሰብ ያለ ነው። ይህ መመሪያ አንድ የመገናኛ ብዙኀን ባልደረባ የሚገጥሙዋቸውን ተግዳሮቶች በሙሉ አይዳስስም፤ እንዲሁም እኛ ባቀረብናቸው ሁሉም ምክረ ሃሳቦች እንደማይስማሙም ግልጽ ነው።

ይኹን እንጂ ሁለት እውነቶችን ለማስታረቅ በብርቱ ታግለናል። ቀዳሚው እነዚህ ጥቃቶች እንስካልተሰነዱ ድረስ የሚቆሙበት አንዳችም መንገድ የለም። ሁለተኛው ደግሞ ወሲባዊ ጥቃት የደረሰበት እያንዳንዱ ግለሰብ ታሪኩ የግሉ ነው፤ የእኛ አይደለም።

ከዚህ በኋላስ?

ይህንን መመሪያ ያዘጋጀነው ውይይትን እና ግንዛቤን ለመፍጠር በማሰብ ነው። እንድናጋራው የተዘጋጀ ነው። እባክዎ ይህንን መመሪያ በማንበብ ለሚጠቀም ሁሉ ያሰራጩ።

የእርስዎን ግብረ መልስ እንጠብቃለን እንዲሁም ወደፊት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ዝግጁ ነው።

ስለ ዳርት ማዕከል ስራዎች የበለጠ ለማወቅ የሚፈልጉ ከሆነ፣ እባክዎን የኢሜል ዝርዝሩ ላይ እዚህ ይመዝገቡ።

አስተዋጽኦ እና ምስጋናዎች

ይህ መረጃ እንዴት እንደተዘጋጀ ያንብቡ

ተጨማሪ ይመልከቱ ያነሰ ይመልከቱ

ይህ መረጃ”፡ አሰቃቂ እና ግጭትን በሚዘግቡ ጋዜጠኞች እና የፊልም ሰሪዎች ትብብር የተቋቋመ ዳርት ሴንተር አውሮጳ በተሰኘው ጥምረት የተዘጋጀ ነው። ስለዚህየመጀመርያው ምስጋና ላለፉት አመታት በማዕከሉ ውስጥ ለተደረጉ ውይይቶች አስተዋጽኦ ላደረጉ ሁሉ መቅረብ አለበት። ዋናው የማደራጀት እና የጽሑፍ ቡድን ጋቪን ሪዝሳሚራ ሻክልእስቲፈን ጁክስጁሊያና ሩህፉስሌዝሊ ቶማስ እና ክርስቲና ላምብ ያቀፈ ነበር።

በቀጥታ ምክክራችን ላይ ለተሳተፉት ሁሉ እናመሰግናለን።

ይህን ፕሮጀክት መፈጸም የተቻለው የዩናይትድ ኪንግደም በየውጭ፣ የኮመንዌልዝ እና የልማት ጽህፈት ቤት፣ በግጭት ውስጥ የሚደረጉ የፆታ ጥቃትን የመከላከል  ተቋም ባበረከተው የገንዘብ ድጋፍ ነው።

WHAT OTHERS HAVE SAID

Read what others have said about these guidelines.

See more See less

“Quis vel eros donec ac odio. Quis enim lobortis scelerisque fermentum dui. Tellus orci ac auctor augue mauris augue. Lacus luctus accumsan tortor posuere ac ut. Curabitur vitae nunc sed velit. Fringilla ut morbi tincidunt augue interdum. Nibh cras pulvinar mattis nunc sed. Vulputate odio ut enim blandit volutpat. Sed augue lacus viverra vitae congue eu. Scelerisque eleifend donec pretium vulputate sapien nec sagittis aliquam. Quam quisque id diam vel.”

ዳርት ማዕከል በአውሮፓ
የማሕበሩ የምዝገባ ቁጥር በኢንግላንድ እና በዌልስ፤ 1172731
እባክዎ ያግኙን። አስተያየትዎን መስማት እንፈልጋለን