ምስሎቹ አይጠፉም፤ በእይታ ምርጫዎች ይጠንቀቁ
ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ሲዘግቡ፣ የሚያደርጓቸው የእይታ ምርጫዎች - በተቀረጹ ቀረጻዎች ወይም በፎቶግራፎች ላይ - ሁሉም በጣም አስፈላጊ ናቸው።
በተለይ አሁን፣ በዲጂታል ዘመን፣ ምስሎች እየሰሩበት ካለው ታሪክ ያለፈ ረጅም ህይወት አላቸው። ጉዳተኞችን በእይታ እንዴት እንደሚቀርቡ እና ምን እንድምታዎች እንዳሉዋቸው ሙሉ በሙሉ እንዲገነዘቡ በጣም አስፈላጊ ነው። የሚከተለውን ግምት ውስጥ ማስገባት አለብዎት፡-
- የተጎጂዎችን ማንነት ለመግለጽ የሚያስገድድ ጠንካራ ምክንያት አለ ወይስ በስም-አልባነት መጀመር የበለጠ ደህንነትን ይጠብቃል?
- ፎቶግራፍ ለመነሳት ወይም በቪድዮ ለመቅረጽ ትርጉም ያለው ስምምነት ሰጥተዋል? በማኅበረሰባቸው ውስጥ ሊታዩ የሚችሉትን የማኅበራዊ ሚዲያ ተደራሽነት ተረድተዋል?
- በምስሉ ላይ ባለማወቅ ማንነታቸውን ሊገልጽ የሚችል ነገር አለ?
- በመጨረሻው ቅንብሩ ምቾት እንዲኖራቸው በምስል ስራው ላይ እንዴት እነሱን ማሳተፍ እችላለሁ?
በግልጽ ልናገር – የግጭት አስገድዶ መድፈር ምስሎችና እና የአስገድዶ መድፈር ጉዳተኞችን በስፋት መሰራት እና መታየት አለባቸው። ምንጮችን የሚከላከሉበት፣ አጠቃላይ ነባራዊ ሁኔታን በሚያከብሩ፣ የተጭበረበሩ አመለካከቶችን በማያስቀጥሉበት እና በሚዲያ ኩባንያዎች ለተጎጂዎች እንደ አንዳንድ አስማታዊ elixirs በማያቀርቡበት መንገዶች በተለየ መሰራት አለባቸው።
ኒና በርማን [ሀ]
ምስሎች ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ላይ ጨምሮ የግጭት ዘገባ ዋና አካል ስለሆኑ ከአንባቢዎች ጋር ለመገናኘት አደገኛ መንገዶች ሊሆኑ ይችላሉ። ነገር ግን ተጎጂዎችን መልሶ ለመጉዳት ትልቅ ዕድል አለ፣ ይህም እነሱን ቃለ መጠይቅ ከማድረጋቸው የሚያያዝ አደጋ በላይ ነው።
የምስል እውቅ አባባሎች የተለመዱ ናቸው – ጉዳተኞችን እንደ ተገለሉ እና ግፍ እንደደረሰባቸው፣ ከራሳቸው አካባቢ የተወገዱ እንደሆኑ፣ ወይም በአካል ላይ ከፍተኛ ትኩረትን ማሳየት። በአንዳንድ አጋጣሚዎች፣ ይህ ከቅኝ ግዛት እና ከባርነት የዘለቀው የዘረኝነት ምስል ታሪክ ውስጥም ሊገባ ይችላል። ምስልን የማንበብ ችሎታ መኖር ይህንን ለመረዳት ወሳኝ አካል ነው።
ከዚህም በላይ ምስሎች በዲጂታል ዘመን፣ በተለያዩ መሳሪያዎች ላይ እና በመድረኮች ላይ በቀላሉ ይጋራሉ፣ ይህም ማለት ጉዳተኞች በሩቅ ማህበረሰቦች ውስጥ ቢኖሩም ለረጅም አመታት በእነሱ ሊሰቃዩ ይችላሉ። እ.ኤ.አ. በ1990ዎቹ የባልካን ጦርነቶች ውስጥ ሴቶች መደፈራቸውን ለባሎቻቸው ሳይነግሩ ያገቡባቸው አጋጣሚዎች ነበሩ። ከአስርተ አመታት በኋላ የመዝገብ ቤት ሰነዶች በኢንተርነት ድህረ-ገጾች ላይ ሊገኝ ይችላል የሚል ሀሳብ የነበራቸው ጥቂቶች እንኳን አልነበሩም።
የዲጂታል ዘመን በምስል የሚመሩ ዘገባዎች የሚበዙበት ሁኔታ እየፈጠረ ስለሆነ፡ በአዘጋጆች እና ፎቶግራፍ አንሺዎች ላይ በጣም አስደንጋጭ እና ትኩረትን የሚስብ ምስል እንዲሰሩ የሚያሳድሩት ጫና ከፍተኛ ሊሆን ይችላል። ይህ የጉዳተኞችን አካል ወሲባዊ የማድረግ ወይም አስፈላጊ ባልሆነ መንገድ ማንነታቸውን ማጋለጥን ሊያስከትል ይችላል።
ቀደም ሲል በስምምነት ክፍል ቁ.3 ላይ እንደተብራራው፣ ምንጮችን እንዴት እንደሚገለጹ በሚወስኑ ውሳኔዎች ላይ ማሳተፍ ጥሩ ልምምድ ነው። የያዚዲ ሴቶች በአይ ኤስ ሲደፈሩ የሚዘግቡ ጋዜጠኞች ፊታቸውን ተከናንበው ፎቶ በማንሳት ስማቸው እንዳይገለጽ ዋስትና እንደሚሰጡ ገምተው ነበር፤ ነገር ግን እንደ እውነቱ ከሆነ በማኅበረሰባቸው ውስጥ በቀላሉ በዓይናቸው እና ልዩ በሆኑ ፎጣቸው ተለይተው ይታወቃሉ።
የበለጠ ውጤታማ እና ሥነ ምግባራዊ የእይታ ምርጫዎችን ማድረግ
የፎቶ ጋዜጠኞች ከፍተኛ ተጽዕኖ ያለው ምስል ለማግኘት ብዙ ጊዜ ከቢሯቸው ከሚመጣ ጫና ውስጥ እየሰሩ ቢሆንም፣ ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) የደረሰባቸው ሰዎችን በማይጎዳ መልኩ እና የተለመዱ አባባሎችን በሚስያወግድ መንገድ፣ ጊዜው ጠባብ በሆነበት ጊዜም እንኳን ቢሆን ምስሎች መስራት ይቻላል፤
እያነሷቸው ስላሉት ምስሎች ራስዎን መጠየቅ ያለብዎት አንዳንድ ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው፡-
- የተጎጂዎች ማንኛቸውም ምስሎች ስም-አልባ ይሆናሉ እና የሚገለጹት ይህን ለማድረግ የሚያስችል ጠንካራ ምክንያት ካለ ብቻ ነው በሚል ግምት መጀመር ትችላላችሁ? መድረሻዎ ላይ ከመድረስዎ በፊት ይህንን ከአዘጋጁ ጋር በዝርዝር ለመወያየት ያስቡበት።
- የተጎጂዎችን ማንነት የማያሳዩ ምስሎችን ለመስራት ብዙ ኃይለኛ እና የፈጠራ መንገዶች አሉ። እነዚህን በደንብ አስቀድመው ማሰብ የተሻለ ነው። ምናልባት ሌሎች የተጠቀሙበት የተሳኩ በርካታ መንገዶች በተመለከተ የዲጂታል ማስታወሻ ደብተር ይያዙ።
- ታሪኩ ስለ አስገድዶ መድፈር ከሆነ፣ ተጎጂዋን አካል እንዴት እየገለጹት እንደሆነ ግንዛቤ ይኑሩዎት። ትኩረትን ወደ የትኛው የሰውነት ክፍል እየሳቡ ነው? ስለ ሰውዬው እንደ ወሲባዊ ቁስ የሚወስድ ማንኛውንም አመለካከት እንዴት ማስወገድ ይችላሉ?
- ሰውዬው ብቸኛ ወይም የፈረሰ እንደሆነ የሚጠቁሙ ምስላዊ የተለመዱ አባባሎችን ለማስወገድ ይሞክሩ። በአንዳንድ ሁኔታዎች፣ ከመጠን በላይ መነጠል የታሪኩ እውነታ ሊሆን ይችላል፣ ግን አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች ሰፋ ያለ የድጋፍ ሁኔታ አላቸው – እናም ያንን ማንጸባረቅ የበለጠ ትክክል ነው።
ማንነትን ለመደበቅ አሃዛዊ ቴክኒኮችን እየተጠቀሙ ከሆነ ማደብዘዝ ብቻ ሳይሆን ኦሪጅናል ፒክስሎች ከምስሉ ላይ መወገድ አለባቸው። እንዲሁም፣ ቦታን የሚለይ ፋይል ውስጥ ምንም ሜታዳታ አለመኖሩን ማረጋገጥ አለቦት። ምስሎች በሚነሱበት ጊዜ እነማን ሊኖሩ እንደሚችሉ እና ለምን እንደሆነ ማሰብም አስፈላጊ ነው። ሊታሰብባቸው የሚገቡ አንዳንድ ነጥቦች እነሆ፡-
- ምንጮቹ፡ አንድ ሰው ከእነሱ ጋር እንዲኖር ይፈልጋሉ ወይንስ በዙሪያው መከታተል የማይገባቸው ሰዎች አሉ? ለዘጋቢ ፊልም ሰሪዎች፣ ሰራተኞቹን መቀነስ ያስቡበት።
- ምስሎቹ ከተነሱ በኋላ ስለተነሱበት መንገድ ደስተኛ መሆናቸውን ለማረጋገጥ ለተጎጂዎቹን ለማሳየት ያስቡበት።
- የተጎጂዎች ምስሎቻቸው ለረጅም ጊዜ ሊኖሩ እንደሚችሉ እና በመድረኮች ላይ፣ በራሳቸው ማህበረሰብ ውስጥም ቢሆን መጋራት እንደሚችሉ መረዳታቸውን ያረጋግጡ።
ሥራውን በፍጥነት ለመጨረስ የማትቸኩልባቸው መንገዶች አሉ? የምስሎች ቀረጻ እንዴት እንደሚሆን አስቀድመው መወያየት እና ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ ማብራራት ይችላሉ? በአንድ ጎልማሳ ሰው በኩል እንኳን ቢሆን፡ ልጆች ማንነታቸው እንዲጋራ በፍጹም ፈቃድ መስጠት እንደማይችሉ ያስታውሱ።
የፎቶ ጋዜጠኝነት እና አዘጋጆች
አንድ ፎቶግራፍ አንሺ እነዚህ ሁሉ ነገሮች በጭንቅላታቸው ላይ እንደማይሆኑ ሊረዳ እችላለሁ፣ አዘጋጅ እንደዛ ሲሆን ግን አስደንጋጭ ነው።
ለአዘጋጆች፣ ከታሪካዊ ሁኔታዎች አንፃር የምስል እውቀት ያለው መሆን በተመለከተ የበለጠ የኃላፊነት ስሜት እንዳለ ይሰማኛል።
ኒና በርማን [ሀ]
ፎቶግራፍ አንሺዎች ከተጎጂዎች ጋር ስለሚገናኙ ስለ ምስላዊ ምርጫዎች ውሳኔ ያደርጋሉ። ነገር ግን አዘጋጆች የትኞቹ ምስሎች መነሳት እንዳለባቸው ይሁን ለህዝብ ከመድረሳቸው በፊት ከተሰበሰቡት ምስሎች የትኞቹ እንደሚመሩጡ የመጨረሻ ኃላፊነት አለባቸው። ለውስጣዊ ገጽ ተገቢ ሊሆን የሚችለው – ትርጉም እና ነባራዊ ሁኔታን የሚያካትት – በሽፋን ላይ ወይም በኢንስታግራም ልጥፍ ላይ ብቻውን የሚቆም ሲነጻጸር ሙሉ በሙሉ የተለየ ተጽዕኖ ሊኖረው ይችላል።
አዘጋጆች፣ ከባለሙያዎች በሚገኝ ድጋፍና እና ከሜዳው ጫና ርቆ ስልታዊ በሆነ መንገድ ለማሰብ በሚረዳ ጊዜ ተደግፈው፣ ፎቶግራፍ ሆን ተብሎ ወይም ባለማወቅ የሚጠቅሰውን ምስላዊ ቋንቋ ማጤን አለባቸው። በባርነት ስለየተያዙ ሰዎች የረዥም ጊዜ ታሪክ አለ፣ ለምሳሌ፣ በማደግ ላይ ባሉ አገሮች ውስጥ የሚሰሩ ምስል ሰሪዎች ሊያስወግዱት የሚገባ።
የፎቶ አርታኢዎች ምስልን በሚመለከት ጥቅም ከዋለበት በኋላ ስለሚኖረው ዕድሜ ሳይቀር የመወሰን ስልጣን አላቸው – ፍቃድ አሰጣጥ እና ተደራሽነት – እንዲሁም በማህበራዊ አውታረ መረቦች ጥቅም ላይ ስለሚውሉበት መንገድ።
እንደ አርታኢ፣ ከረጅም ጊዜ የስራ ባልደረቦችዎ ጋር እየሰሩ ወይም በጭራሽ ያላገኟቸው ነፃ ጋዜጠኞችን በማሰማራት ላይ ሊሆኑ ይችላሉ። ስለ ድንበሮች፣ ትርጉም ያለው ስምምነት እና ማንነትን ስለመደበቅ ለአጭር የ10 ደቂቃ ውይይት ጊዜ መስጠት ትልቅ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል። ሊታሰብባቸው የሚገቡ አንዳንድ ነገሮች እነዚህ ናቸው፡-
- በስምምነት ዙሪያ ከፎቶግራፍ አንሺዎች ጋር ትክክለኛ ውይይት አድርገዋል? [ቁ.3 ይመልከቱ]
- ተጎጂዎች እንዲታወቁ አስፈላጊነት አለው? ማንነታቸው እንዳይገለጽ በሚያደርጉበት ጊዜ ምን ዓይነት የእይታ ጥገናዎች ይሰራሉ?
- መግለጫ ጽሑፎች የታሪኩ አካል ስለሆኑ፡ ልክ እንደ ምስሎቹ፣ ሰውየውን ወሲባዊ ማድረግ ወይም ማዋረድ የለባቸውም። ከግጭት ጋር የተያያዘ ወሲባዊ ጥቃት (CRSV) ሰለባ የሆኑ ሰዎችን ምስሎችን የጊዜ ገደብ መስጠት ይችላሉ?
- ለዜና ተቋማት ላይ የማይሸጡ ለአንድ ዘገባ ጥቅም ብቻ የሚውሉ ሊያደርጓቸው ይችላሉ? በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ምስሎችን እንዴት እየተጠቀሙባቸው ነው?
- ለምሳሌ በኢንስታግራም ላይ የተጎጂው ፊት ወይም አካል ማሳየት አለብዎት ወይስ አንድ ግለሰብ ሙሉውን ክብደት እንዲሸከም በማያደርግ መልኩ ታሪኩን የሚያስተዋውቁበት ሌላ መንገድ አለ?
]የግርጌ ማስታወሻዎች፡-
-
ሀ.
ኒና በርማን በቦዝኒያ እና አፍጋኒስታን ግጭቶችን የዘገበች የዘጋቢ ስዕል አንሺ ነች። ለዚህ ፕሮጀክት በተደረገ ምርምር አስተዋፅዖ ያበረከተች ስትሆን፡ በግጭት እና በሰላማዊ ጊዜ የፎቶግራፍ ሥነ-ምግባር ላይ የጻፈች እና በኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት ፕሮፌሰር ነች። ለተጨማሪ፡ እዚህ ይመልከቱ፡ https://dartcenter.org/resources/visual-choices-covering-sexual-violence-conflict-zones